አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ቶተንሀም እና አርሰናል ሴኔጋላዊውን ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊን ለማስፈረም ይፈልጋሉ ሁለቱም ክለቦች ከተጨዋቹ ወኪሎች ጋር ንግግር ማድረግ እንደጀመሩ ተሰምቷል።
ሊቨርፑሎች ከሳውዝሀምተንካስፈረሙት ረጅም አመታትን በአንፊልድ የቆየውን እንግሊዛዊውን አዳም ላላን በክረምቱ በነፃ ሊለቁት ነው ምክንያቱም ተጨዋቹ ኮንትራቱ በዚህ አመት ሲጠናቀቅ ሊቨርፑሎች ለልጁ አዲስ ኮንትራት ለመስጠት ፍላጎት የላቸውም።
ቸልሲዎች የአጥቂ መስመር ችግራቸውን ለመቅረፍ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የሊዮኑን ሙሳ ዴምቤሌን እና የኢንተር ሚላኑን ላውታሮ ማርቲኔዝን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።
ባርሴሎናዎች ለፊሊፕ ኩቲትሆ 80ሚዩ ይፈልጋሉ ይህንን ገንዘብ ለሚያቀርብ ክለብ ልጁን ለመስጠት ፍቃደኛ ናቸው።
£15ሚ. የሚያወጣውን የብሬንትፎርድ የመስመር ተጨዋች ሰኢድ ቤንረህማን ለማስፈረም ሌስተር እና አርሰናሎች ተፋጠዋል።
የቀድሞው የአርሰናል ቶተንሀም እና ማን ሲቲ አጥቂ ኢማኑዬል አዲባየር ለፓራጓዩ ኦሎምፒያ ክለብ ለመጫወት መስማማቱ ታውቋል።
በጥር የዝውውር ዶርትመንድን የተቀላቀለው የፊት መስመር አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ የጥር ወር የቡንደስ ሊጋው ምርጥ ተጫዋች በመባል ተመርጧል።
ኢቫንዛሞራ አርትሮ ቪዳል በክረምቱ ወደ ቀድሞ አሰልጣኙ አንቶኒዮ ኮንቴው ጁቬንቱስ ለማምራት እንደተዘጋጀ ይፋ አድርጓል።
ቸልሲ እና ማንዩናይትድ በእንግሊዛዊው የቦሩሲያ ዶርትመንድ የመስመር አጥቂ ዳጀን ሳንቾ ዝውውር ላይ ተፋጠዋል።ዛሬ በወጡ መረጃዎች መሰረት ዩናይትዶች ከቸልሲ የተሻለ ሂሳብ ለማቅረብ ዝግጁ ሆነዋል።
No comments:
Post a Comment