Sunday, February 16, 2020

የዕለተ ሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                          አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)



ምንም እንኳን ማንቸስተር ሲቲ ለተከታታይ ሁለት አመታት በሻምፒዮንስ ሊግ እንዳይሳተፍ ቢታገድም ፔፕ ጋርዲዮላ ግን በክለቡ ይቆያል።
(Mirror)





የቀድሞው የጁቬንትስ ሌጀንድ አሌሀንድሮ ዴልፔይሮ ፔፕ ጋርዲዮላ አሮጊቷን ቢይዝ ደስተኛ እንደሚሆን ተናግሯል።ፔፕ ማውሩዚዮ ሳሪን ተክቶ ቱሪን ሊከትም እንደሚችል በስፋት እየተነገረ ነው።
(Sky Sports)





የእንግሊዛዊው ራሂም ስተርሊንግ ወኪል ደንበኛው በክለቡ ላይ ሙሉ ትኩረቱን እንደሚያደርግ እና ስሙ ከዝውውር ጋር በስፋት በመነሳቱ እንደማይረበሽ ተናግሯል።
(Mirror)





ኦሌ ጉናር ሶልሻየር ማንቸስተር ዩናይትድ ለቀጣዩ አመት በሻምፒዮንስ ሊግ ሊያሳትፈው የሚችለውን ውጤት ባያስመዘግብም ክረምት ላይ ያለውን የዝውውር ዕቅድ እንደማይቀይረው ያስባል።
(Mirror)





ሶልሻየር ከቻይናው ክለብ ሻንጋይ ሺኖዋ በውሰት ማንቸስተር ዩናይትድን የተቀላቀለው ናይጄሪያዊው አጥቂ ኦዲዮን ኤግሃሎ በቋሚነት ኦልድ ትራፎርድ ሊቀር እንደሚችል ተናግሯል።
(Manchester Evening News)





ባርሴሎና የኢንተር ሚላኑን አርጀንቲናዊ አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ ከገንዘብ በተጨማሪ አንቱዋን ግሬዝማንን ለዝውውሩ አካል ሊያደርግ ይችላል።የላውታሮ ማርቲኔዝ የዝውውር ሂሳብ £92ሚ. ገደማ ነው።
(Sun)





ማንቸስተር ሲቲ በሻምፒዮንስ ሊግ የተጣለበት ዕገዳ የሚጸና ከሆነ በርካታ ወሳኝ ተጨዋቾቹን ሊያጣ እንደሚችል ይጠበቃል።
(Telegraph)






አር ቢ ሌብዚኽ ጀርመናዊውን አጥቂ ቲሞ ዋርነር ለማዘዋወር ሊቨርፑል ምንም አይነት ንግግር በቀጥታ ከነሱ ጋር እንዳላደረገ ተናግረዋል።ዋርነር በዚህ አመት 20 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።
(Mirror)






No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...