Monday, February 17, 2020

የዕለተ ሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

በሪያል ማድሪድ በጥብቅ እየተፈለገ የሚገኘው ራሂም ስተርሊንግ ትኩረቱ ለማንችስተር ሲቲ ብቻ እንደሆነ ተናገረ ።




የቀድሞ ጣሊያናዊ ኮከብ ዴል ፔሮ ፔፕ ጋርዲዮላ ትክክለኛው ለጁቬንቱስ የሚሆን አሰልጣኝ እንደሆነ ተናግሯል። የሲቲን ቅጣት ተከትሎ ፔፕ ከኢትሀድ መልቀቁ አይቀሬ ነው።





ማንችስተር ሲቲዎች አርብ ምሽት ለሁለት አመት ከአውሮፓ ውድድሮች መታገዱ ይታወሳል ፥  እናም ሲቲዎች ውሳኔውን ለማስቀየር ለይግባኝ ሰሚው አካል አቤቱታ አቅርበዋል።





የኦስማን ዴምቤሌን ጉዳት ተከትሎ ባርሴሎናዎች በላሊጋው አወዳዳሪ አካል በመጪው 15 ቀናት ውስጥ ተጨዋች እንያዘዋውሩ ፍቃድ አግኝተዋል።




በኖርዊች ጥሩ የሚባል አመትን እያሳለፈ የሚገጀው ካንትዌል በሌላኛው የእንግሊዝ ክለብ ሊቨርፑል ራዳር ውስጥ ገብቷል።ኖርዊቾች ከተጨዋቹ እስከ £30m ይፈልጋሉ።




ባርሴሎናዎች የወሳኝ ተጨዋቻቸውን ግልጋሎት ለሶስት ሳምንታት እንደማያገኙ ተሰምቷል። በላሊጋው ቅዳሜ እለት ተጎድቶ ከሜዳ የወጣው ጆርዲ አልባ ባርሴሎና በቀጣይ ሳምንት በቻምፒየንስ ሊግ እና በኤልክላሲኮ የአልባን ግልጋሎት አያገኝም።





በቅዳሜው ምሸት ጨዋታ ከስብስብ ውጭ ተደርገው የነበሩት ክሊያን ምባፔ እና ኔይማር ፒኤስጂ ዶርትመንድን ለመግጠም ከሚያመራው ስብስብ ውስጥ ተካተዋል።





ጀምስ ማዲሰን ዩናይትድን መቀላቀል ይፈልጋል። እንደሱ ፍላጎት ብቻ ቢሆን ኖሮ ከአመት በፊት ዩናይትድን ሊቀላቀል ይችል ነበር ተብሏል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...