Tuesday, February 18, 2020

የዕለተ ረቡዕ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች



ትናንት በሻምፒዮንስ ሊግ በተደረገ ጨዋታ ቦሩሲያ ዶርትመንድ ፔዤ ሲረታ ኤርሊንግ ሀላንድ የማሸነፊያዎቹን ሁለቱንም ግቦች አስቆጥሯል።ኖርዌጅያኑ አጥቂ ለጀርመኑ ክለብ በሰባት ጨዋታዎች 11 ግቦችን ነው ከመረብ ያሳረፈው።



ሪያል ማድሪዶች በጥር የዝውውር መስኮት ያስፈረሙትን ሬነርን ትናንት ከሰአት በይፋ አስተዋውቀውታል። ሬነር በራዎል በሚሰወጥነው ሁለተኛ ቡድን ካስቴላን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል።




ሰንሁንግ ሚን በጉዳት ምክንያት በቀጣይ ሳምንታት የጆዜን ቡድን አያገለግልም።ከሀሪ ኬን ጉዳት ቡሀላም ለጆዜ ወሳኝ የሚባል ግልጋሎትን እየሰጠ የሚገኘው ሚን ቶተንሀም በቀጣይ በቻምፒየንስ ሊግ ደርሶ መልስ እንዲሁም በፕሪሚየር ሊጉ ከቸልሲ፣ ወልቭስ እና ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታዎች ያመልጡታል።




ዚያችን ለቸልሲ አሳልፈው የሰጡት አያክሶች ትላልቅ ተጨዋቾቻቸው ከትልልቅ የአውሮፓ ክለቦች ጋር ስማቸው እየተነሳ ይገኛል። በክረምቱም ብዛት ሊለቁባቸው ይችላሉ። በክረምቱ አያክስን ይለቃሉ ከተባሉት ውስጥ ዶኒ ቫንድቢክ በዩናይትድ እና ማድሪድ ግብ ጠባቂው ኦናና በቸልሲ ዳኒ ብሊንድ በአርሰናል  ቬልትማን፣ ታግሊያፊኮ እና ኔሬስ በተለያዩ ክለቦች የዝውውር ራዳር ውስጥ ገብተዋል።





የቀድሞ የባርሴሎና የማን.ሲቲ እንዲሁም የኦሎምፒያኮስ ተጨዋች ኮትዲቫራዊው ያያ ቱሬ በዚህ ሳምንት ወደ አንድ ክለብ ሊቀላቀል መሆኑ ተሰምቷል።ቱሬ በሳምንቱ መጨረሻ የብራዚሉን ክለብ ቦታፎጎ እንደሚቀላቀል ተሰምቷል።




ኤቨርተን እና ቶተንሀም በሮማ በውሰት ድንቅ አመትን በግሉ እያሳለፈ የሚገኘውን ንብረትነቱ የማንችስተር ዩናይትድ የሆነውን ክሪስ ስሞሊንግ ለማስፈረም ይፈልጋሉ።




ትናንት የዴምቤሌን መጎዳት ተከትሎ ሌላ ተጨዋች ለማስፈረም ጥያቄ አቅርበው ተቀባይነት ያገኙት ባርሴሎናዎች £17m የውል ማፍረሻ ያለውን የ28 አመቱን ማርቲን ብሬይዝዋይትን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል።




የዩናይትድ ባለቤቶች የሆኑት የግሌዘር ቤተሰቦች ክለቡን የሚሸጡት 1ቢሊዮን ፓውንድ ከቀረበላቸው ብቻ መሆኑን አሳውቀዋል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...