ሌስተር ሲቲዎች በክረምቱ ከኮንትራት ነፃ የሚሆነውን የሊቨርፑሉን አዳም ላላናን በነፃ ለማስፈረም ድርድር መጀመራቸው ይፋ ተደርጓል።
በቶተንሀሙ ጨዋታ ላይ ጉዳት ደርሶበት ጨዋታውን ሳይጨርስ ከሜዳ ተቀይሮ የወጣው የማንችስተር ሲቲው ራሂም ስተርሊንግ ከጉዳቱ በማገገም ልምምድ ጀምሯል። ለሲቲዎችም መልካም ዜና ተብሏል። ሲቲ በቀጣይ ሳምንት በቻምፒየንስ ሊግ ማድሪድን ሲገጥም የስተርሊንግን ግልጋሎት ያገኛል።
አርሰናሎች የ18 ወራት ኮንትራት ብቻ በአርሰናል የሚቀረውን ወጣቱን ተጨዋች ባካዮ ሳካ የተሻለ ኮንትራት በማቅረብ በኢምሬት ለማቆየት ፍላጎት አላቸው። ተጨዋቹ በዩናይትድ ቸልሲ ባየርን ሙኒክ ይፈለጋል።
ላዚዮዎች በቸልሲ የመሰለፍ እድል የተነፈገውን እና በዚህ አመት መጨረሻ ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን ኦሊቨር ዡሩድን ለማስፈረም ኮንትራት አቅርበውለታል።
ባርሳዎች £18m በማውጣት የሌጋኔሱን አጥቂ ማርቲን ብሬዝዌይትን ዝውውር ለማዘዋወር ከጫፍ ደርሷል። ዝውውሩን በቀናት ውስጥ እንደሚጨርሱት ተነግሯል።
የአር ቢ ሌብዢኩ ፈረንሳዊው ተከላካይ ዳዮት ኦፓሜካኖ በተለያዩ ክለቦች ራዳር ውስጥ ገብቷል። በጥሩ የዝውውር መስኮት አርሰናልን ይቀላቀላል ሲባል ቢቆይም አሁን ላይ ተጨዋቹ ባርሴሎና እና ባየርንሙኒክ ጭምር ይፈለጋል።
በቀጣይ ዩናይትድ የሚሸጥ ከሆነ አዲሶቹ ባለቤቶች ለስታድየም እድሳት እስከ 200ሚ.ፓ ሊያወጡ እንደሚችሉ ተዘግቧል። እንደ ዘገባው ከሆነ በስታድየሙ የተለያዩ የፍሳሽ ማሶገጃዎች ችግር እንዳለባቸውና አይጦችም በብዛት እንደሚገኙ ተገልጿል።
No comments:
Post a Comment