Thursday, February 20, 2020

የዕለተ አርብ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች

ትናንት ምሽት በዩሮፓ ሊግ በርካታ ጨዋታዎች የተደረጉ ሲሆን አርሰናል እና ኢንተር ሚላን ሲያሸንፉ ማንቸስተር ዩናይትድ አቻ ወጥቷል።



ሙሳ ዴንቤሌ ከቸልሲ ይልቅ ዩናይትድን መምረጡ ተሰምቷል።ፈረንሳዊው የሊዮን አጥቂ በክረምቱ ዩናይትድን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል።




ኢንተር ሚላኖች በዚህ አመት ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን እና እስካሁን በናፖሊ አዲስ ኮንትራት ያልፈረመውን ድረስ መርተንስን በክረምቱ በነፃ ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረዋል።




በትላልቅ የአውሮፓ ክለቦች አይን ውስጥ የገባው የባየርን ሌቨርኩሰኑ ካይ ሀቬርትዝ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ ትልቅ ክለብ ሊያመራ እንደሚችል የክለቡ ሀላፊዎች ፍንጭ ሰተዋል።





አርሰናሎች ለ24  አመቱ ጀርመናዊ ተከላካይ 40ሚ.ዩሮ ለመክፈል ፍላጎት አላቸው።በባየርን ሌቨርኩሰን ድንቅነቱን እያሳየ የሚገኘው ጆናታን ታህ በተለያዩ ክለቦች ቢፈለግም ማረፊያው ግን ኢምሬትስ ሊሆን እንደሚችል በሰፊው እየተነገረ ነው።





ጁቬንቱሶች በቀጣይ ክረምት የአጥቂ መስመራቸውን ለማጠናከር ፍላጎት አላቸው። እንደ ቱቶ ስፖርት ዘገባ ጁቬዎች ፊት መስመራቸውን ለማጠናከር ብራዚላዊውን የማን.ሲቲ አጥቂ ገብርኤል ጂሰስ እና በፒኤስጂ በውሰት የሚገኘውን ማውሮ ኢካርዲን ማስፈረም ይፈልጋሉ።




ዩናይትዶች ጄደን ሳንቾን እንደሚያስፈርሙት ተማምነዋል ነገር ግን ዩናይትዶች ሳንቾን ለማግኘት የግድ ቀጣይ አመት ቻምፒየንስ መሳተፍ የግድ ይላቸዋል።




አርሰናሎች የቀድሞ ኮከባቸውን ሳንቲ ካዞርላን ለማምጣት እና ተጫውቶ ደጋፊውን እንዲሰናበት ለማድረግ እያጤኑበት ይገኛል።ከዚህም በተጨማሪ ለካዞሮላ በአርሰናል ቤት አዲስ ሚና ሊሠጡት ፍላጎት አላቸው።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...