Friday, February 21, 2020

የዕለተ አርብ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

በሰኞ የብሪጅ ጨዋታ ላይ ከእረፍት በፊት ተቀይሮ ከሜዳ የወጣው የቸልሲው ኒጎሎ ካንቴ በጉዳት ምክንያት ከ3-4 ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ላምፓርድ ይፋ አድርጓል።




ጁቬንቱሶች ፖግባን ለማዘዋወር አዲስ የዝውውር ፓኬጅ ለዩናይትድ አዘጋጅተዋል።ጁቬዎች £50+ራምሴን በመስጠት ፖግባን ለመውሰድ ይፈልጋሉ።




በበርካታ የአውሮፓ ክለቦች እይታ ውስጥ የገባው የሬይኑ ወጣት አማካይ ኤዱዋርዶን ለማስፈረም የዚዳኑ ማድሪድ ክትትል ጀምረዋል።




የጣሊያኖቹ ጁቬዎች እና ኢንተር ሚላኖች የቸልሲውን ጣሊያናዊ የግራ መስመር ተጨዋች ኤመርሰን ፓልሚየርሚን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።





ኢንተሮች የተከላካይ ክፍላቸውን ለማጠናከር የቬሮናውን ተከላካይ ማራሽ ኩምቡላ ለማስፈረም ፍላጎት አለው ፥ ሊቨርፑሎችም ተከላካዩን ይፈልጉታል።




ማንችስተር ሲቲ እና ባርሴሎና የኢንተር ሚላኑን ተከላካይ ሚላን ስክሪኒየር ማዘዋወር ከፈለጉ ኢንተሮች እስከ 90ሚዩ መክፈል እንደሚኖርባቸው ነግረዋቸዋል።




የሊቨርፑሉ ጆርዳን ሄንደርሰንን ለቀጣይ ሶስት ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ተረጋግጧል።




ዩናይትድ ወሳኝ ተጨዋቾችን ከጉዳት መልስ አግኝቷል።ማክቶሚናይ እና ቱአንዛቤ ወደ ሙሉ ልምምድ ተመልሰዋል ማክቶሚናይ ለእሁዱ ጨዋታ ዝግጁ ነው በተጨማሪም ፖግባ ወደ ልምምድ ተመልሷል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...