Thursday, February 27, 2020

የዕለተ አርብ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                            አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)



የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ሌጀንድ ፖል ስኮልስ ቀያይ ሰይጣኖቹ ብሩኖ ፈርናንዴዝን ማስፈረማቸው ትክክል እንደነበር ተናግሯል።ስኮልስ የብሩኖ መምጣት ማን ዩናይትድን ለመ'ታየት የሚያጓጓ አድርጎታል ሲልም አክሏል።ፖርቱጋላዊው አማካይ ቲያትር ኦፍ ድሪምስ ከከተመ አንስቶ ሸጋ ጊዜን በማሳለፍ ላይ ይገኛል።
(Goal)





የቼልሲው አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ስምንት ተጨዋቾችን ከክለቡ ማሰናበት ይሻል።ኬፓ አሪዛባልጋ ፣ ጆርጊንሆ እና ሮዝ ባርክሌይ ደሞ ከተጨዋቾቹ ዝርዝር ውስጥ የሚገኙ ናቸው ሲል ሰን አስነብቧል።
(Sun)





ማንቸስተር ዩናይትድ ከሶስት አመታት በፊት 2017 ላይ የባየርን ሙኒኩን ካናዳዊ የግራ መስመር ተከላካይ አልፎንሶ ዳቪስ በ£2ሚ. የማዘዋወር ዕድል ገጥሞት ነበር።
(Times, subscription required)





የጅማት ጉዳት አጋጥሞት እስከ አመቱ መጨረሻ ከሜዳ እንደሚርቅ ሲነገርለት የነበረው እንግሊዛዊው የቶተንሃም አጥቂ ሀሪ ኬን ከታቀደው ቀደም ብሎ ሚያዚያ ወር ላይ ወደ ሜዳ ይመለሳል።
(Sun)





የአርሰናሉ ፈረንሳዊ አጥቂ አሌክሳንደር ላካዜት የ18 አመቱ የቡድን አጋሩ ቡካዮ ሳካን የወቅቱ ምርጡ ወጣት ተጨዋች ሲል ገልጾታል።እንግሊዛዊው የግራ መስመር ተከላካይ ሸጋ ጊዜን በመድፈኞቹ ቤት በማሳለፍ ላይ ይገኛል።
(Evening Standard)




በባየርን ሙኒክ አሳማኝ በሆነ መልኩ በሜዳው የተረታው ቼልሲ የክረምቱ የውድድር መስኮት አዳዲስ ተጨዋቾችን ለማዘዋወር ይሰራል።ሀኪም ዚያችን ከወዲሁ ማግኘቱን ያረጋገጠው ላምፓርድ ቀጣዩ እቅዱ የሊዮኑን ሀውሴም አውራ ማዘዋወር ነው።
(Tuttomercato)





ማንቸስተር ሲቲ የተከላካይ መስመሩን ለማጠናከር የኤቨርተኑን ሜሰን ሆልጌት የማዘዋወር ዕቅድ አለው።ፔፕ ጋርዲዮላ ከኤምሪክ ላፖርቴ ጋር የሚያጣምረውን ሁነኛ ተከላካይ በማሰስ ላይ ነው።
(The Mirror)




ማንቸስተር ሲቲ የፋይናንስ ጨዋነት ደንብን በመተላለፉ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የነጥብ ቅነሳ ቅጣት ሊደረግበት እንደሚችል እየተዘገበ ነው።ሲቲ በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ለሁለት ተከታታይ አመታት በሻምፒዮንስ ሊግ እንዳይካፈል መቀጣቱ ይታወሳል።
(Mail)





ሊቨርፑል ለኔዘርላንዳዊው የ28 አመት ተከላካይ ቨርጅል ቫን ዳይክ የዓለማችን ውዱ ተከላካይ ተከፋይ የሚያደርገውን አዲስ ኮንትራት ሊያቀርብለት ነው።
(Mirror)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...