Sunday, February 16, 2020

የዕለተ እሁድ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ




አሮጊቶቹ ፖግባን በክረምቱ ወደ ቱሪን ለመመለስ ትልቅ ፍላጎት አሳይተዋል።ከአውሮፓ ዋንጫ በፊት የፖግባን ዝውውር ለመጨረስ ራቢዮትን እና ራምሴን የዝውውሩ አካል ለማድረግ ፍላጎት አላቸው።




የፈረንሳይ ሚዲያዎች ከሰአት በሰበር ዜና መልክ ስለ ዳጆን ሳንቾ አዲስ ዜና ይዘው ወተዋል። ሳንቾ በተለያዩ ክለቦች ቢፈለግም ቸልሲዎች ተጨዋቹን ለማዘዋወር ከዶርትመንድ ጋር ንግግር ጀምረዋል።




ዩናይትዶች ሶልሻየርን ሚያሰናብቱት ከሆነ የቀድሞ የጁቬንቱስ አለቃ ማክሲሚሊያኖ አሌግሪን ለመቅጠር ፍላጎት እንዳላቸው ተሰምቷል።አሌግሪ ከዩናይትድ በተጨማሪ የፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂም ይፈልገዋል።





የሌስተር ሲቲው አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ ከቀድሞ ልጁ ጋር ለመገናኘት ፍላጎት አሳይተዋል።ሮጀርስ ፊቱን ወደ አርሰናሉ ግራ መስመር  ተከላካይ ኬራን ቴርኒ ላይ አርገዋል። እንደ ምክንያት የተነሳው ደሞ ሌስተሮች ቤን ቺልዌልን በክረምቱ ማጣታቸው አይቀሬ ስለሆነ ነው።





ሊቨርፑሎች ጀርመናዊውን የአርቢ ሌብዢኩን አጥቂ ቲሞ ዋርነር ለማስፈረም ከሌብዢክ ጋር ድርድር መጀመሩ ተሰምቷል።ሊቨርፑሎች ለተጨዋቹ እስከ £50m ለመክፈል ፍቃደኛ ናቸው።




ኢንተር ሚላኖች ላውታሮ ማርቲኔዝን ለባርሴሎና የሚሸጡ ከሆነ በምትኩ አንቱዋን ግሪዝማንን ይፈልጋሉ።





ወደ ዩናይትድ ይገባል ሲባል የቆየው ማውሪዚዮ ፖቸቲንሆ ሳይታሰብ ቀጣይ ማረፊያው እዛው ማንችስተር ከተማ ማን.ሲቲ ሊሆን ይችላል።እንደ መረጃዎች ከሆነ ፔፕ ሲቲ ለሁለት አመት ከአውሮፓ ውድድሮች መታገዱን ተከትሎ በኢትሀድ የመቆየት እድሉ ጠባብ ነው።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...