አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
የዩናይትድ ባለ ስልጣኖች ፖል ፖግባን በመልቀቅ በምትኩ የሌስተሩን ጀምስ ማዲሰን እና የአስቶንቪላውን ጃክ ግሪሊሽን ለማስፈረም እንደሚፈልጉ ታውቋል።
አርሰናሎች ለፔር ኤምሪክ ኦባምያንግ የመሸጫ ሂሳብ አውተውለታል።አርሰናሎች ማንኛውም £70m ይዞ ለሚመጣ ክለብ የ30 አመቱን ኮከብ ለመልቀቅ ፍቃደኛ ናቸው።
ሊቨርፑሎች ሮበርት ፈርሚንሆን ሚያጡ ከሆነ በሱ ምትክ የቤኔፊካውን አጥቂ ካርለስ ቪኒሲየስት ለማስፈረም ይፈልጋሉ።ተጨዋቹ በቤኔፊካ ውል ማፍረሻው £100m ሲሆን ሊቨርፑሎች ግን £50m በመክፈል እንደሚወስዱ ተማምነዋል።
ዚነዲን ዚዳን ለሶስት ወራት ከሜዳ እርቆ የቆየው ኤደን ሀዛርድ ነገ በበርናባው ማድሪድ ሴልታቪጎን ሲገጥም ወደ ሜዳ እንደሚመለስ አረጋግጧል።
እንደ ላጋዜታዴሎ ስፖርት ዘገባ ከሆነ ጁቬንቱሶች በዚህ አመት መጨረሻ ውሉ የሚጠናቀቀውን ፈረንሳዊው አማካይ ብለስ ማቲዩዲን ውል ለማራዘም ድርድር መጀመሩ ታውቋል።
ምባፔ እና ኔይማር ፒኤስጂ ዛሬ ምሽት ከአሚነስ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ ስብስብ ውጪ ሆነዋል። ምክንያቱ ደግሞ ፒኤስጂ ከቀናት ቡሀላ ከዶርትመንድ ጋር ለሚያደርገው የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ መሆኑ ታውቋል።
ቸልሲ እና አርሰናል አይናቸውን ስፔናዊው ኮከብ ላይ ኢስኮ አልካሴር ላይ ጥለዋል። ማድሪዶች ለኢስኮ እስከ £65m ይፈልጋሉ።ተጨዋቹ በክረምት መልቀቁ አይቀሬ ነው።
No comments:
Post a Comment