አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
አርሰናል እና ቼልሲ ስፔናዊውን የሪያል ማድሪድ አማካይ ኢስኮ በ£63ሚ. ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።ሪያል ማድሪድ በክረምት ታላላቅ ዝውውሮችን የመፈጸም ዕቅድ ስላለው ከወዲሁ ኢስኮ የመሸጥ ፍላጎት አለው።
(Sun)
ትናንት ማንቸስተር ሲቲን ከአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለሁለት ተከታታይ አመታት ማገዱን የአውሮፓ እግር ኳስ ማሐበር ይፋ አድርጓል።የUEFAን የተለያዩ ህጎች የጣሰው ሲቲ £30ሚ. የገንዘብ ቅጣትም ተጥሎበታል።
(Mirror)
ያለ አግባብ ተጨዋቾችን በማስፈረሙ ከሻምፒዮንስ ሊግ ለሁለት አመት የታገደው ማንቸስተር ሲቲ በእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበርም ቅጣት ሊጣልበት እንደሚችል እየተነገረ ነው።ቅጣቱም በሊጉ ላይ የነጥብ ቅነሳ እንደሚሆን ተጠቁሟል።
(Star)
ፖል ፖግባ ክረምት ላይ ከማንቸስተር ዩናይትድ የመውጣት ፍላጎት አለው።ሆኖም ማንቸስተር ዩናይትድ ለዝውውሩ ከፈላጊ ክለቦች የጠየቀው የተጋነነ ሒሳብ ህልሙን እንዳያሳካ ሳንካ ሊሆንበት ይችላል።
(Guardian)
ኢንተር ሚላን አርጀንቲናዊውን አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ የሚያጣ ከሆነ የአርሰናሉን ጋቦናዊ አጥቂ ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ ማዘዋወር ይፈልጋል።
(Star)
ማንቸስተር ዩናይትድ ፈረንሳዊውን የሊዮን አጥቂ ሙሳ ዴምቤሌ ለማዘዋወር £60ሚ. አሰናድቷል።ኦሌ ጉናር ሶልሻየር የ23 አመቱን ተጨዋች አጥብቆ ይሻዋል።
(Star)
ቶተንሃም የኖርዊች ሲቲውን ተከላካይ ቤን ጎድፍሬይ ለማዘዋወር ፍላጎት አለው።የ22 አመቱ እንግሊዛዊ የዝውውር ሒሳቡ £50ሚ. ገደማ ነው።
(Express)
ፓሪሰን ዤርመን በተለይ በሪያል ማድሪድ በጥብቅ የሚፈለገውን ፈረንሳዊውን አጥቂ ኪሊያን ምባፔ በፓርክ ደ ፕሪንስ ለማቆየት አዲስ ኮንትራት ሊያቀርብለት ነው።እንደ ሚረር ዘገባ ከሆነ አዲሱ ኮንትራት ለ21 አመቱ አጥቂ በአመት £41ሚ. ያስገኝለታል።
(Mirror)
No comments:
Post a Comment