አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
የአውሮፓ ታላላቆቹ ክለቦች ሪያል ማድሪድ እና ሊቨርፑል የኢንተር ሚላኑን አማካይ ማርሴሎ ብሮዞቪችን ለማስፈረም ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።
የቱርኩ ቤሺክታሽ ግብፃዊውን መሀመድ ኤኔኒን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከአርሰናል በውሰት ማስፈረማቸው ይታወሳል ፥ እናም ቤሺክታሾች ዝውውሩን ቋሚ ለማድረግ ከአርሰናል ጋር ንግግር ለማድረግ ዝግጁ ናቸው።
ኢንተርሚላኖች ሆላንዳዊውን የዩናይትድ ወጣት ተጨዋች ታሂት ቾንግን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል። ወጣቱ ቾንግ በዚህ አመት መጨረሻ ኮንትራቱ የሚጠናቀቅ ይሆናል። በዚህም ኢንተሮች ልጁን በነፃ ያገኙታል።
ፒኤስጂዎች ወጣቱን ግብ ጠባቂ ዲን ሄንደርሰንን ከዩናይትድ ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው። በአሁን ሰአት ሄንደርሰን ለሼፍልድ በውሰት እየተጫወተ ይገኛል። ከፒኤስጂ በተጨማሪም ቸልሲ፣ቶተንሀም እና በውሰት ሚጫወትበት ሼፍልድ የልጁ ፈላጊ ናቸው።
በዩናይትድ በጥብቅ ሚፈለገው እንግሊዛዊው የአስቶንቪላ ተጨዋች ጃክ ግሪሊሽ በክረምቱ ወደ ዩናይትድ ማምራት እንደሚፈልግ ለክለብ ጉዋደኞቹ ነግሮዋቸዋል።
አርሰናሎች በክረምቱ ባየርን ሙኒክን መልቀቁ እውን ለመሆን የተቃረበውን ፈረንሳዊውን ኮረንቲን ቶሊሶን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ሊያስፈርሙት ይፈልጋሉ።
ሪያል ማድሪዶች በተለያዩ ክለቦች የሚፈለገውን የኢንተር ሚላን አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀመሩ።ኢንተሮች ተጨዋቹን የመሸጥ ፍላጎት የላቸውም።
No comments:
Post a Comment