አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ማንቸስተር ዩናይትድ ፈረንሳዊውን የሊዮን አጥቂ ሙሳ ዴምቤሌ ለማዘዋወር £60ሚ. አሰናድቷል።ኦሌ ጉናር ሶልሻየር የ23 አመቱን ተጨዋች አጥብቆ ይሻዋል።
(Star)
ቶተንሃም የኖርዊች ሲቲውን ተከላካይ ቤን ጎድፍሬይ ለማዘዋወር ፍላጎት አለው።የ22 አመቱ እንግሊዛዊ የዝውውር ሒሳቡ £50ሚ. ገደማ ነው።
(Express)
ፓሪሰን ዤርመን በተለይ በሪያል ማድሪድ በጥብቅ የሚፈለገውን ፈረንሳዊውን አጥቂ ኪሊያን ምባፔ በፓርክ ደ ፕሪንስ ለማቆየት አዲስ ኮንትራት ሊያቀርብለት ነው።እንደ ሚረር ዘገባ ከሆነ አዲሱ ኮንትራት ለ21 አመቱ አጥቂ በአመት £41ሚ. ያስገኝለታል።
(Mirror)
በሻምፒዮንስ ሊግ በደርሶ መልስ በሪያል ማድሪድ የሚሸነፍ ከሆነ ማንቸስተር ሲቲ ሊያሰናብተው እንደሚችል ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግሯል።ማን ሲቲ በዘንድሮው አመት ከወትሮው በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉም ደካማ ጊዜን በማሳለፍ ላይ ይገኛል።
(Guardian)
ሪያል ማድሪድ አርጀንቲናዊውን አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ ከኢንተር ሚላን ለማዘዋወር የውል ማፍረሻውን €120ሚ. ለመክፈል ዝግጁ ነው።የ22 አመቱ ተጨዋች በዘንድሮው አመት እያሳየ ባለው ድንቅ አቋም በበርካታ ጉምቱ የአውሮፓ ክለቦች አይን ውስጥ ገብቷል።
(TyC Sports)
ሜሲ በባርሴሎና ደስተኛ መሆኑን የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኙ ስካሎኒ ተናገረ።ሰሞኑን ሜሲ ከባርሴሎና ሊለቅ እንደሚችል በስፋት ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል።
(Goal)
በባርሴሎና ያለው ቆይታ ጥያቄ ምልክት ውስጥ የገባው ኢቫን ራኪቲች በጁቬንትስ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር ቢጫወት ደስተኛ እንደሚሆን ተናግሯል።ራኪቲች ከጁቬንትስ በተጨማሪ በኢንተር ሚላን ፣ በማንቸስተር ዩናይትድ እና ፓሪሰን ዤርመን ይፈለጋል።
(Goal)
ጁቬንትስ ብራዚላዊውን አጥቂ ዊልያን ከቼልሲ ለማዘዋወር ፍላጎት ቢኖረውም ዊልያን ግን ከማውሩዚዮ ሳሪ ጋር በዚህ ፍጥነት ዳግም መስራት አይሻም።
(Express)
No comments:
Post a Comment