አቅራቢ- ኢብራሒም ሙሐመድ
ዩናይትድ እና ሊቨርፑል የስታድየም ማስፋፊያ ሊያደርጉ ነው። ቀያይ ሰይጣኖቹ ተጨማሪ 1,500 ተመልካች የሚይዝ መቀመጫዎችን ለመስራት ሲያስቡ ሊቨርፑሎች ተጨማሪ 7,000 መቀመጫ ወንበሮችን ለመስራት አስበዋል።
በጉዳት ምክንያት ከዚህ አመት ውድድር ውጭ ነው ሲባል የሰነበተው የባርሴሎና አጥቂ ሉዊስ ሱዋሬዝ ከተባለለት ቀን በፊት ወደ ልምምድ ሊመለስ ይችላል። እንደ መረጃዎች ከሆነ ሱዋሬዝ በሚያዚያ ወር ውስጥ ልምምድ እንደሚጀምር ተሰምቷል።
ኤደን ሀዛርድ ከሶስት ወር ቆይታ ቡሀላ ወደ ሜዳ ሊመለስ ነው።ማድሪዶች እሁድ ከሴልታቪጎ ለሚያደርጉት ጨዋታ ዝግጁ ነው።እንዲሁም ከሲቲ ላለባቸው የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ዝግጁ ነው።
ቸልሲ ሀኪም ዚያችን ማስፈረሙን አረጋግጧል። ተጨዋቹ የቸልሲ ንብረት መሆኑን ቸልሲም አያክስም ይፋ አድርገዋል።ቸልሲ ለተጨዋቹ £40m ለአያክስ ሲከፍል የክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ሲከፈት ተጨዋቹ በይፋ የቸልሲ ንብረት ይሆናል።
አርሰናሎች ለማቲዮ ጉንዶዚን አዲስ ኮንትራት ሊያቀርቡለት ነው።ጉንዶዚን በአርሰናል ኮንትራት ቢኖረውም አርሰናሎች የወደፊቱን በማሰብ ተጨማሪ ኮንትራት ሊያቀርቡለት ነው።
ዳጀን ሳንቾ በክረምት ዶርትመንድን መልቀቁ እውን መሆኑን ስካይ ስፖርት አስነብቧል። ቀጣዩ ጥያቄ የተጨዋቹ ማረፊያ የት ነው ሚለው ነው፥ ተጨዋቹን ቸልሲ እና ዩናይትድ በጥብቅ ይፈጉታል። ነገር ግን ቸልሲዎች ዚያችን ስላገኙ ሳንቾን እንደተዉት እርግጥ ሆኗል።ስለሆነም የተጨዋቹ ቀጣይ ማረፊያ ዩናይትድ ሊሆን ይችላል።
የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ጆዜፕ ባርቶሚዮ በመጪው ክረምት ኔማርን ለማስፈረም ዝግጁ ሆነዋል።እንደ ካታላን ጋዜጦች ከሆነ ባርቶሚዮ ኔማርን ለማስፈረም ሁለት ትላልቅ ሚባሉ ተጨዋቾችን ለመሸጥ ዝግጁ ሆነዋል።
No comments:
Post a Comment