Tuesday, December 10, 2019

የረቡዕ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                     አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)

ሎዛ አበራ በአንድ ጨዋታ 7 ግብ አስቆጠረች

በማልታ የሴቶች ሊግ እጅግ አስደናቂ እንቅስቃሴ እያደረገች ያለችው ኢትዮጵያዊቷ ኮከብ ሎዛ አበራ ትናንት የእርሷ ክለብ ቢሪክሪካ ኢብርኒንስን 17 ለ  0 ሲያሸነፍ ብቻዋን 7 ግብ ያስቆጠረች ሲሆን በዚህም መሰረት በአጠቃላይ በዘንድሮ አመት ለክለቡ 18ተኛ ግቧን አስቆጥራለች።

ሎዛ አበራ በኢትዮጵያ የሴቶች ሊግ አስገራሚ እንቅስቃሴ ታደርግ እንደነበር ይታወሳል።
( Ethio Women Sport)


✅ትናንት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ በተደረጉ ጨዋታዎች የተመዘገቡ ውጤቶች

➡️ናፖሊ 4-0 ጌንክ
➡️ሳልዝቡርግ 0-2 ሊቨርፑል

➡️ቦሩሲያ ዶርትሙንድ 2-1 ስላቪያ ፕራሃ
➡️ኢንተር ሚላን 1-2 ባርሴሎና

➡️ቤኔፊካ 3-0 ዜኒት ፒተርስበርግ
➡️ሊዮን 2-2 ሌብዚሽ

➡️አያክስ 0-1 ቫሌንሲያ
➡️ቼልሲ 2-1 ሊል

✅ዛሬ የሚደረጉ ጨዋታዎች መርሃግብር
➡️ክለብ ብሩዥ ከ ሪያል ማድሪድ - 5:00
➡️ፓሪሰን ዤርመን ከ ጋላታሳራይ - 5:00

➡️ባየርን ሙኒክ ከ ቶተንሃም - 5:00
➡️ኦሎምፒያኮስ ከ ዝቬዝዳ - 5:00

➡️ዳይናሞ ዛግሬቭ ከ ማን ሲቲ - 2:55
➡️ሻካታር ዶኔስክ ከ አታላንታ - 2:55

➡️አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ሎኮሞቲቭ ሞስክ - 5:00
➡️ባየርን ሊቨርኩሰን ከ ጁቬንትስ - 5:00



ሊቨርፑል ፥ ማንቸስተር ሲቲ እና ቼልሲ የፓሪሰን ዤርመኖቹን ብራዚላዊው የ27 አመት ኮከብ ኔይማር እና የ20 አመቱን ፈረንሳዊ ኮከብ ኪልያን ምባፔ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ የገቡ የእንግሊዝ ክለቦች ናቸው።ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎናም ሌሎቹ ፈላጊዎች ናቸው፡፡
(Le Parisien, via Mirror)



ትናንት ምሽት ከናፖሊ የተሰናበቱት ጣሊያናዊው አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ከወደ እንግሊዝ ከወዲሁ ፈላጊ አግኝተዋል።አንጋፋውን አሰልጣኝ ለመቅጠር ጥያቄ ያቀረበው በቅርቡ ማርኮ ሲልቫን ያሰናበተው ኤቨርተን ነው፡፡
(Telegraph)



ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድኑን ለማጠናከር አዲስ የተከላካይ መስመር ተጨዋች ይፈልጋል።ዋነኛው እቅዱ ደግሞ ፈረንሳዊውን የባርሴሎና የ26 አመት ተከላካይ ሳሙኤል ኡምቲቲ ወደ ኤቲሀድ ማምጣት ነው።የማይሳካ ከሆነ ደግሞ ኔዘርላንዳዊውን የበርንማውዝ ተከላካይ ናታን አኬ እንደ ሁለተኛ ምርጫ ይዘዋል።
(L’Equipe, via TEAMtalk)


እንግሊዛዊው የ21 አመት ተከላካይ ፊካዮ ቶሞሪ በቼልሲ ለረዥም ጊዜ እንዲቆይ አዲስ ኮንትራት ቀርቦለታል።
(Goal)


ወደ ጣሊያን ሊሄድ እንደሚችል በሰፊው ሲነገርለት የነበረው አንጋፋው የ38 አመት ስዊድናዊ አጥቂ ዝላታን ኢብራሒሞቪች ሳይጠበቅ ወደ እንግሊዝ ሊመለስ እንደሚችል ተነግሯል።የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን ለዝላታን አመታዊ £4ሚ. ደሞዝ አቅርቦለታል፡፡
(Express)



ማን ዩናይትድ በጥብቅ ሲፈልገው የነበረው የሌስተር ሲቲው የ23 አመት እንግሊዛዊ አማካይ ጄምስ ማዲሰን በኪንግ ፓወር ለተጨማሪ አመታት ለመቆየት አዲስ ኮንትራት ሊፈርም ነው።
(Mirror)


አንቶኒዮ ኮንቴ በቼልሲ ሳለ የነበሩትን ሶስት ተጨዋቾች ወደ ኢንተር ሚላን ለማምጣት ይፈልጋል።ተጨዋቾቹም ስፔናዊያኑ የግራ መስመር ተከላካይ ማርኮስ አሎንሶ እና አጥቂው ፔድሮ እንዲሁም ፈረንሳዊው አጥቂ ኦሊቪየር ዢሩ ናቸው፡፡
(Goal.com)



ባርሴሎና አርጀንቲናዊውን የ22 አመት የኢንተር ሚላን አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ ለማዘዋወር ለጣሊያኑ ክለብ €100ሚ. አቅርቧል።
(ESPN)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...