✅ዛሬ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።መርሃ ግብሮቹን እነሆ
➡️ናፖሊ ከ ጌንክ - 2:55➡️ሳልዝቡርግ ከ ሊቨርፑል - 2:55
➡️ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከ ስላቪያ ፕራሃ - 5:00
➡️ኢንተር ሚላን ከ ባርሴሎና - 5:00
➡️ቤኔፊካ ከ ፓሪሰን ዤርመን - 5:00
➡️ሊዮን ከ ሌብዚሽ - 5:00
➡️አያክስ ከ ቫሌንሲያ - 5:00
➡️ቼልሲ ከ ሊል - 5:00
ፓሪሰን ዤርመን የአለማችን ውዱ ተጨዋች ኔይማር ከክለቡ የሚለቅበት ከሆነ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የ27 አመቱ ሴኔጋላዊ ኢንተርናሽናል ሳዲዮ ማኔ ከሊቨርፑል ማዘዋወር ይፈልጋል ።
(France Football via Sport Witness)
ማን ዩናይትድ በዘንድሮ አመት አስደናቂ ጊዜን እያሳለፈ ላለው ስኮትላንዳዊው አማካይ ስኮት ማክቶሚናይ አዲስ ኮንትራት አቅርቦለታል።ቀያይ ሰይጣኖቹ ለተጨዋቹ ሳምንታዊ £60,000 ደሞዝም አሰናድተውለታል፡፡
(Sun)
ማርኮ ሲልቫን ባለፈው ሳምንት ያሰናበተው የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን ከአርሰናል የተሰናበቱትን ኡናይ ኤምሬን በአሰልጣኝነት ለመሾም ፍላጎት አለው።ስፔናዊው አሰልጣኝ ግን ለጊዜው እረፍት እንደሚፈልጉ እየተናገሩ ነው።
(Sky Sports)
ማን ዩናይትድ ለረዥም ጊዜ ሲፈልገው የነበረውን የቶተንሃሙን አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለማሳካት ከወዲሁ እየሰራ ነው።ከጆዜ ሞሪንሆ ጋር እምብዛም ያልተግባባው የ27 አመቱ አማካይ ከስፐርስ መውጣቱ አይቀሬ ይመስላል።
(90min)
የባርሴሎናው ፕሬዝደንት ጆዜፍ ባትቶሚዮ የማን ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ወደ ካታላኑ ክለብ መመለስ ከፈለገ በየትኛውም ጊዜ በራችን ክፍት ነው ብለዋል።ፔፕ የአሰልጣኝነቱን አስደናቂ ጊዜ በካምፕ ኑ እንዳሳለፈ ይታወቃል።
(La Repubblica, via Goal)
ባርሴሎና የውል ማፍረሻው €111ሚ. የሆነውን የኢንተር ሚላኑን ድንቅ አርጀንቲናዊ አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ለድርድር ወደ ሚላን ያቀኑ ሰዎችም አሉ ከካታላኑ ክለብ።
(Sport - in Spanish)
የማን ዩናይትድ የበላይ አመራሮች ለኦሊ ጉናር ሶልሻየር ተረጋግቶ ስራውን እንዲሰራ እና እርሱን የማባረር እቅድ እንደሌላቸው ነግረውታል።ማን ዩናይትድ ስሙ ከስፋት ከቀድሞው የቶተንሃም አሰልጣኝ ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ ጋር ሲያያዝ ቆይቷል።
(Mail)
አርሰናል በሮማ የሚገኘውን ክሪስ ስሞሊንግን ለማዘዋወር ከኢንተር ሚላን እና ጁቬንትስ ከፍተኛ ፉክክር ገጥሞታል።እንግሊዛዊው ተከላካይ ከማን ዩናይትድ በውሰት ነው ለሮማ የተሰጠው።
(Mirror)
No comments:
Post a Comment