Monday, December 9, 2019

የሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

ነገ በሻምፒዮንስ ሊግ ኢንተር ሚላን ባርሴሎናን በሚያስተናግድበት ጨዋታ ሜሲ እንደማይሰለፍ ታውቋል።የስድስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው አርጀንቲናዊ ጥበበኛ ወደ ሚላን ከቡድኑ ጋር አልተጓዘም።ያልተጓዘበት ምክንያት ግን እስካሁን ይፋ አልሆነም።
(BBC)



በውሰት ከማን ዩናይትድ ለሮማ የተሰጠውን እንግሊዛዊውን ተከላካይ ክሪስ ስሞሊንግ ለማስፈረም አርሰናል ጥረት ማድረግ ጀምሯል።የ30 አመቱ ተከላካይ በኤቨርተን እና በሌስተር ሲቲም ይፈለጋል።
(Mirror)



በበርካታ ሐያላን የአውሮፓ ክለቦች ዘንድ አይን ውስጥ የገባውን ኖርዌያዊውን አጥቂ ኤርሊንግ ሃላንድ ለማዘዋወር ጁቬንትስ ጥረት ማድረግ ጀምሯል።የውል ማፍረሻው €30ሚ. የሆነውን የሬድ ቡል ሳልዝቡርግ አጥቂ ለማዘዋወር  በዋናነት ማን ዩናይትድ እንደሚፈልግ ተደጋግሞ ተዘግቧል።
(Corriere dello Sport - in Italian)



ከባየርን ሙኒክ የተሰናበተው ክሮኤሽያዊው አሰልጣኝ ኒኮ ኮቫች ዛሬ አርሰናል ዌስት ሀምን በሚገጥምበት ጨዋታ እንደሚታደም ይጠበቃል።ኮቫች ምናልባትም ቀጣዩ የአርሰናል አሰልጣኝ ሊሆን ይችላል፡፡
(Goal)



ጆዜ ሞሪንሆ በማን ዩናይትድ ሳሉ ቁልፍ ተጨዋቻቸው የነበረውን ቤልጄሚያዊውን አማካይ ማርዋን ፌይላኒ ከቻይናው ክለብ ሻንጋይ ኤስ.አይ.ፒ.ጂ ወደ ቶተንሃም እንዲመጣላቸው ይፈልጋሉ።
(DH Net - in French)


የጥዋቱ ላመለጣችሁ ከዚህ በታች እነሆ :

ምንም እንኳን ባርሴሎና አርጀንቲናዊውን አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የማዘዋወር ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖረውም በአንቶኒዮ ኮንቴ ስር አስደናቂ ጊዜን እያሳለፈ ያለው ማርቲኔዝ ግን በኢንተር ሚላን መቆየትን ይፈልጋል፡፡
ማርቲኔዝ በዘንድሮው አመት በሴሪ ኤው በ13 ጨዋታዎች ስምንት ግብ አስቆጥሯል።
(Sport Italia)




ሪያል ማድሪድ ኮሎምቢያዊውን አጥቂ ሀሜስ ሮድሪጌዝ እና ዌልሳዊውን ጋሬዝ ቤል ለማን ዩናይትድ በመስጠት በምትኩ የ26 አመቱን ፈረንሳዩ አማካይ ፖል ፖግባ ለመውሰድ ለቀያይ ሰይጣኖቹ ጥያቄ አቅርቧል።
(Eldesmarque via Sunday Express)



በፔፕ ጋርዲዮላ ስር በምክትልነት እየሰራ የሚገኘው ማይክል አርቴታ ቀጣዩ የአርሰናል አሰልጣኝ እንደሚሆን እየተዘገበ ነው።መድፈኞቹ ኡናይ ኤምሪን ካሰናበቱም በኋላ በጊዜያዊው አሰልጣኝ ፍሬዲ ሊዩምበርግ አስቸጋሪ ጊዜን እያሳለፉ ይገኛሉ።
(Sunday Telegraph)



በአመቱ መጨረሻ በፓሪሰን ዤርመን ያለው ኮንትራት የሚያበቃውን ኡራጋዊውን አጥቂ ኤዲንሰን ካቫኒ በድጋሚ ወደ ኔፕልስ ለማምጣት አወዛጋቢው የናፖሊው ፕሬዝደንት ኦላሪዮ ደ ላውረንቲስ ይፈልጋሉ።
(Il Mattino)


ከጆዜ ሞሪንሆ መምጣት በኋላ ቶተንሃም ከናፖሊው ድንቅ ተከላካይ ኩሊባሊ ጋር መነጋገር ጀምሯል።የቶቢ ኤልደርዊልድ እና ያን ቬርቶገን ኮንትራት በክረምት ስለሚገባደድ ስፐርስ ከወዲሁ ሴኔጋላዊውን ተከላካይ ከጣሊያኑ ክለብ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ጥረት ጀምሯል።
(El Desmarque)


አርጀንቲናዊው የአታላንታ ዩናይትድ ተጨዋች ኤስኩዌል ባርኮ በበርካታ ሐያላን የአውሮፓ ክለቦች አይን ውስጥ ገብቷል፡፡አርሰናል ፥ ማን ዩናይትድ ፥ ኢንተር ሚላን ፥ ሮማ  ፥ ሊል እና ቫሌንሲያ ተጨዋቹን ለማስፈረም ፉክክር ውስጥ ናቸው።
(Sport)



የባርሴሎናው አማካይ ካርሎና አሌና በጥር ወር የዝውውር መስኮት የካታላኑን ክለብ እንደማይለቅ ተናግሯል።
"ውሳኔው ሙሉ ለሙሉ የኔ ነው የሚሆነው።ከአመራሮቹ ጋር ጥሩ ግንኙነት አለኝ የምፈልገውንም እንድመርጥ እንደሚፈቅዱ እርግጠኛ ነኝ፡" ብሏል።
(Sport)



በሳምንቱ መጨረሻ ላዚዮ ጁቬንትስን 3ለ1 በረታበት ጨዋታ ግብ ያስቆጠረውን ሰርቢያዊውን አማካይ ሰርጂ ሚሊንኮቪች ዳቪች ለመመልከት የማን ዩናይትድ መልማዮች በሜዳው ተገኝተው ነበር።ከጨዋታው በኋላ ስለ ጉዳዩ የተጠየቀው ሳቪች "በአሁኑ ሰዓት ላዚዮ ነኝ።የወደፊቱን ግን አላውቅም" ብሏል።
(Gazzetta dello Sport)



ዘንድሮ አስደናቂ ጊዜን እያሳለፈ ያለው የብሬንደን ሮጀርሱ ሌስተር ሲቲ ትናንትም ከሜዳው ውጪ አስቶን ቪላን 4ለ1 የረታ ሲሆን ጄሚ ቫርዲ ሁለት ግብ አስቆጥሯል።እንግሊዛዊው አጥቂ በዚህ አመት በተከታታይ ለስምንተኛ ጨዋታ ነው ግብ ያስቆጠረው።ሌስተር ሻምፒዮን በነበረበት አመት ቫርዲ በተከታታይ ለአስራ አንድ ጨዋታ ግብ ማስቆጠሩ የሚታወስ ሲሆን በሊጉ በተከታታይ ብዙ ጊዜ ግብ በማስቆጠርም ሪከርዱ የእርሱ ነው።
(Opta)



 ከትናንት በስቲያ ምሽት በኤቲሀድ ተደርጎ በነበረው ማንቸስተር ደርቢ የማን ዩናይትዶቹ ጄሴ ሊንጋርድ እና ፍሬድ ላይ የዘረኝነት ጥቃት ተሰንዝሮባቸዋል።ከጨዋታው በኋላው ወዲያውኑ ማን ሲቲ ያንን ያደረገውን ደጋፊ ከዚህ በኋላ ስቴዲየም እንዳይገባ እገዳ እንደጣለበት ይፋ አድርጓል።
 ፍሬድ ከESPN Brazil ጋር በነበረው ቆይታ
"እንዳለመታደል ሆኖ አሁንም ኋላቀር ማህበረሰብ ውስጥ ነን።2019 ሆኖም እንደዚህ አይነት ሰዎች አሉ።ሰዎቹ ተመለከቱኝ።ከዛም አንዱ ላይተር ወርውሮ መቶኛል።እኔ ግን ለዛ ግድ ሳይሰጠኝ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ነው የሞከርኩት።" ብሏል።
(Bbc)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...