አቅራቢ-አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ምንም እንኳን ባርሴሎና አርጀንቲናዊውን አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የማዘዋወር ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖረውም በአንቶኒዮ ኮንቴ ስር አስደናቂ ጊዜን እያሳለፈ ያለው ማርቲኔዝ ግን በኢንተር ሚላን መቆየትን ይፈልጋል፡፡
ማርቲኔዝ በዘንድሮው አመት በሴሪ ኤው በ13 ጨዋታዎች ስምንት ግብ አስቆጥሯል።
(Sport Italia)
ሪያል ማድሪድ ኮሎምቢያዊውን አጥቂ ሀሜስ ሮድሪጌዝ እና ዌልሳዊውን ጋሬዝ ቤል ለማን ዩናይትድ በመስጠት በምትኩ የ26 አመቱን ፈረንሳዩ አማካይ ፖል ፖግባ ለመውሰድ ለቀያይ ሰይጣኖቹ ጥያቄ አቅርቧል።
(Eldesmarque via Sunday Express)
በፔፕ ጋርዲዮላ ስር በምክትልነት እየሰራ የሚገኘው ማይክል አርቴታ ቀጣዩ የአርሰናል አሰልጣኝ እንደሚሆን እየተዘገበ ነው።መድፈኞቹ ኡናይ ኤምሪን ካሰናበቱም በኋላ በጊዜያዊው አሰልጣኝ ፍሬዲ ሊዩምበርግ አስቸጋሪ ጊዜን እያሳለፉ ይገኛሉ።
(Sunday Telegraph)
በአመቱ መጨረሻ በፓሪሰን ዤርመን ያለው ኮንትራት የሚያበቃውን ኡራጋዊውን አጥቂ ኤዲንሰን ካቫኒ በድጋሚ ወደ ኔፕልስ ለማምጣት አወዛጋቢው የናፖሊው ፕሬዝደንት ኦላሪዮ ደ ላውረንቲስ ይፈልጋሉ።
(Il Mattino)
ከጆዜ ሞሪንሆ መምጣት በኋላ ቶተንሃም ከናፖሊው ድንቅ ተከላካይ ኩሊባሊ ጋር መነጋገር ጀምሯል።የቶቢ ኤልደርዊልድ እና ያን ቬርቶገን ኮንትራት በክረምት ስለሚገባደድ ስፐርስ ከወዲሁ ሴኔጋላዊውን ተከላካይ ከጣሊያኑ ክለብ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ጥረት ጀምሯል።
(El Desmarque)
አርጀንቲናዊው የአታላንታ ዩናይትድ ተጨዋች ኤስኩዌል ባርኮ በበርካታ ሐያላን የአውሮፓ ክለቦች አይን ውስጥ ገብቷል፡፡አርሰናል ፥ ማን ዩናይትድ ፥ ኢንተር ሚላን ፥ ሮማ ፥ ሊል እና ቫሌንሲያ ተጨዋቹን ለማስፈረም ፉክክር ውስጥ ናቸው።
(Sport)
የባርሴሎናው አማካይ ካርሎና አሌና በጥር ወር የዝውውር መስኮት የካታላኑን ክለብ እንደማይለቅ ተናግሯል።
"ውሳኔው ሙሉ ለሙሉ የኔ ነው የሚሆነው።ከአመራሮቹ ጋር ጥሩ ግንኙነት አለኝ የምፈልገውንም እንድመርጥ እንደሚፈቅዱ እርግጠኛ ነኝ፡" ብሏል።
(Sport)
በሳምንቱ መጨረሻ ላዚዮ ጁቬንትስን 3ለ1 በረታበት ጨዋታ ግብ ያስቆጠረውን ሰርቢያዊውን አማካይ ሰርጂ ሚሊንኮቪች ዳቪች ለመመልከት የማን ዩናይትድ መልማዮች በሜዳው ተገኝተው ነበር።ከጨዋታው በኋላ ስለ ጉዳዩ የተጠየቀው ሳቪች "በአሁኑ ሰዓት ላዚዮ ነኝ።የወደፊቱን ግን አላውቅም" ብሏል።
(Gazzetta dello Sport)
ዘንድሮ አስደናቂ ጊዜን እያሳለፈ ያለው የብሬንደን ሮጀርሱ ሌስተር ሲቲ ትናንትም ከሜዳው ውጪ አስቶን ቪላን 4ለ1 የረታ ሲሆን ጄሚ ቫርዲ ሁለት ግብ አስቆጥሯል።እንግሊዛዊው አጥቂ በዚህ አመት በተከታታይ ለስምንተኛ ጨዋታ ነው ግብ ያስቆጠረው።ሌስተር ሻምፒዮን በነበረበት አመት ቫርዲ በተከታታይ ለአስራ አንድ ጨዋታ ግብ ማስቆጠሩ የሚታወስ ሲሆን በሊጉ በተከታታይ ብዙ ጊዜ ግብ በማስቆጠርም ሪከርዱ የእርሱ ነው።
(Opta)
ከትናንት በስቲያ ምሽት በኤቲሀድ ተደርጎ በነበረው ማንቸስተር ደርቢ የማን ዩናይትዶቹ ጄሴ ሊንጋርድ እና ፍሬድ ላይ የዘረኝነት ጥቃት ተሰንዝሮባቸዋል።ከጨዋታው በኋላው ወዲያውኑ ማን ሲቲ ያንን ያደረገውን ደጋፊ ከዚህ በኋላ ስቴዲየም እንዳይገባ እገዳ እንደጣለበት ይፋ አድርጓል።
ፍሬድ ከESPN Brazil ጋር በነበረው ቆይታ
"እንዳለመታደል ሆኖ አሁንም ኋላቀር ማህበረሰብ ውስጥ ነን።2019 ሆኖም እንደዚህ አይነት ሰዎች አሉ።ሰዎቹ ተመለከቱኝ።ከዛም አንዱ ላይተር ወርውሮ መቶኛል።እኔ ግን ለዛ ግድ ሳይሰጠኝ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ነው የሞከርኩት።" ብሏል።
(Bbc)
No comments:
Post a Comment