Friday, December 6, 2019

የዕለተ አርብ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

                    አቅራቢ-አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ዛሬ ምሽት 4:45 በጣሊያን ሴሪ ኤ የሊጉ መሪ ኢንተር ሚላን በሜዳው ሳንሲሮ ጁሴፔ ሜይዛ ሮማን ያስተናግዳል።በዘንድሮው አመት በአንቶኒዮ ኮንቴ መሪነት አስደናቂ ጊዜን እያሳለፉ ያሉት ናራዙሪዎቹ በላውታሮ ማርቲኔዝ እና ሮሜሮ ሉካኩ የፊት መስመር መሪነት ዛሬም ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ይጠበቃል።

በሌላ ጨዋታ በስፔን ላሊጋ ምሽት 5:00 ሰዓት ላይ ቪያሪያል አትሌቲኮ ማድሪድን ያስተናግዳል።



ሌስተር ሲቲ አሰልጣኙን ብራንደን ሮጀርስ ለተጨማሪ አመታት በኪንግ ፓወር ለማቆየት አዲስ ኮንትራት አቅርቦላቸዋል።በዘንድሮው አመት አስደናቂ ቡድን የገነቡት ሮጀርስ በቅርቡ ኡናይ ኤምሬን አሰናብቶ በጊዜያዊነት ፍሬዲ ሊዩምበርግን በሾመው አርሰናል ይፈለጋሉ።
(Telegraph)



ትናንት ምሽት አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫን ያሰናበተው የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን በፖርቱጋላዊው ሰው ምትክ የሻንጋይ ኤስ.አይ.ፒጂውን ቪክቶር ፔሬራ ለመሾም እየሰራ ነው፡፡
(Mail)



ስሙ ከበርካታ ክለቦች ጋር እየተያያዘ የሚገኘው የቀድሞው የቶተንሃም ሆትስፐር አሰልጣኝ ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ ባየርን ሙኒክን በዚህ ወቅት እንደማያሰለጥን ታምኙ የጀርመን ጋዜጣ ቢልድ ከሰፊ ሀተታ ጋር ገልፇል።
(Bild - in German - subscription required)




የቀድሞው የጁቬንትስ አሰልጣኝ ማሲሚሊያኖ አሌግሪ እስከ መጪው ክረምት ወደ አሰልጣኝነት እንደማይመለሱ ተናግረዋል።ጣሊያናዊው አሰልጣኝ በአሁኑ ወቅት እንግሊዘኛ ቋንቋን እየተማሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል።ይህም ቀጣይ ማረፊያቸው ከእንግሊዝ ክለቦች አንዱ ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ሰጪ ነው ተብሏል።
(ESPN)




በሳምንቱ አጋማሽ ኦልድ ትራፎርድ ላይ ማን ዩናይትድ የጆዜ ሞሪንሆን ቶተንሃም ማሸነፉን ተከትሎ ተጨዋቾቹ ለበላይ አመራሮቹ ኦሊ ጉናር ሶልሻየር እንዳይባረር አስተያየት ሰጥተዋል።
(Times - subscription required)



ማይክል አርቴታ ስሙ ከአርሰናል ጋር መያያዙን ተከትሎ ወደ ሰሜን ለንደኑ ክለብ የሚያቀና ከሆነ ፔፕ ጋርዲዮላ የቀድሞውን ዶምኒክ ቶሬንት በምክትል አሰልጣኝነት እንዲሾምለት ይፈልጋል።
(Sun)




ማን ዩናይትድ አሁንም ዴንማርካዊውን አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን የማዘዋወር ፍላጎት አለው።ቀያይ ሰይጣኖቹ የ27 አመቱን የጨዋታ ቀማሪ ከዚህ በፊት ለማዘዋወር ሞክረው ባይሳካላቸው አሁን ግን ኤሪክሰን በተለይ ከጆዜ ሞሪንሆ ጋር ባለመስማማቱ ዝውውሩ ሊሳካ ይችላል።
(Mirror)




ሊዮኔል ሜሲ ሴኔጋላዊው የሊቨርፑል ኮከብ ሳዲዮ ማኔ በባሎንዶር ሽልማት አራተኛ ደረጃ ማግኘቱ እንደሚያንሰው ተናግሯል።

"ማኔ አራተኛ ደረጃ ላይ መቀመጡ በጣም አሳፋሪ ነው።"

"በኔ ግምት በዚህ አመት በርካታ ምርጥ ተጨዋቾች ነበሩ።ለዛም ነው አንድ ተጨዋች ብቻ መምረጥ የሚከብደው።ነገር ግን እኔ የምመርጠው ሳዲዮ ማኔን ነው ምክንያቱም እንደሱ አይነት ተጨዋች ነው የምወደው" በማለት ነው የተናገረው ሊዮ።

ማኔ ባሳለፍነው  ሰኞ በነበረው የባሎንዶር ሽልማት ከሊዮኔል ሜሲ፥ ቨርጅል ቫን ዳይክ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ በመቀጠል አራተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወዳል።

ሴኔጋላዊው ኮከብ ትናንት በመርሲዳይድ ደርቢ ኤቨርተን ላይ አንድ ግብ በማስቆጠር ሁለት አሲስት በማድረግ ድንቅ ምሽት አሳልፏል

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...