Wednesday, December 4, 2019

የረቡዕ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

                        አቅራቢ-አብዱልቃድር በሽር (የሪሀና ልጅ)

በሚመጣው የጥር ወር የዝውውር መስኮት ካልተሸጠ በክረምት በቦስማን ህግ መሰረት ወደ ፈለገበት ክለብ የመሄድ መብት ያለውን ኤሪክሰንን ቶተንሃም ለመሸጥ ይፈልጋል።ስፐርስ የ27 አመቱን ዴንማርካዊ አማካይ ብሎ ለሚመጣ ክለብ ከ£40ሚ. በታችም ቢሆን የመሸጥ ፍላጎቱ አላት።
(Evening Standard)





በቶተንሃም አምስት አመት ከግማሽ ካሳለፈ በኋላ የተሰናበተው አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ ማን ዩናይትድን የማሰልጠን ፍላጎት እንዳለው ተገልፇል።ቀያይ ሰይጣኖቹ ወጣቱን አሰልጣኝ ባለፉት አመታት ሊሾሙት ፈልገው እንዳልተሳካላቸው ይታወሳል።
(Manchester Evening News)



ማን ሲቲ በዘንድሮው አመት እጅግ የተሳካ ጊዜን በኢንተር ሚላን እያሳለፈ የሚገኘውን አርጀንቲናዊውን አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ የማዘዋወር ፍላጎት አለው።ባርሴሎናው የ22 አመቱ ኮከብ ፈላጊ ነው።
(Sky Sports Italia, via Calciomercato - in Italian)




የ33 አመቱ ፈረንሳዊ አጥቂ ኦሊቪየ ዢሩ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ከቼልሲ መሰናበት እንደሚፈልግ ለአመራሮቹ አሳውቋል።
(Evening Standard)



ከሜጀር ሊግ ሶከሩ ክለብ ኤል.ኤ ጋላክሲ ከለቀቀ በኋላ ማረፊያው ያልታወቀው የቀድሞው ለማን ዩናይትድ አጥቂ ዝላታን ኢብራሂሞቭች ወደ ጣሊያን እንደሚያመራ አሳውቋል።የ38 አመቱ ስዊድናዊ ክለቡን ግን አልጠቀሰም።
(GQ Italia - in Italian)


ከባሎንዶር ሽልማት ጋር በተያያዘ ቫን ዳይክ ሮናልዶ ላይ መሳለቁን ተከትሎ ሮናልዶም የመልስ ምት በሚመስል መልኩ አስየያየቱን ሰጥቷል።
"ሊዮኔል ሜሲ ባሎንዶርን ስላሸነፍክ እንኳን ደስ አለህ።የባሎንዶር ስነ-ስርዓቱን ለመጀመሪያ ጊዜ የታደምከውም እንኳን ደስ አለህ" ብሏል ሮናልዶ።


ዛሬ ካፍ የአመቱ ምርጥ ተጨዋቾችን ለመምረጥ ዕጩዎቹን አስር ተጨዋቾች ይፋ አድርጓል።ዕጩዎቹ የሚከተሉት ናቸው
1.አንድሬ ኦናና - አያክስ (ካሜሮን)
2.ሀኪም ዛይች - አያክስ (ሞሮኮ)
3.ኢስማኢል ቤናኪር - ኤሲ ሚላን (አልጄሪያ)
4.ካሊዱ ኩሊባሊ - ናፖሊ (ሴኔጋል)
5.ሙሐመድ ሳላህ - ሊቨርፑል (ግብፅ)
6.ኦዲዮን ኤግሃሎ - ሻንጋይ ሺኖዋ (ናይጄሪያ)
7.ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ - አርሰናል (ጋቦን)
8.ሪያድ ማህሬዝ - ማን ሲቲ (አልጄሪያ)
9.ሳዲዮ ማኔ - ሊቨርፑል (ሴኔጋል)
10.ዩሱፍ ቢላሊ - አል አህሊ (አልጄሪያ)


ዛሬ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሚደረጉ ጨዋታዎች መርሃ ግብር :

ቼልሲ 🆚 አስቶን ቪላ ➡️ 4:30
ሌስተር ሲቲ 🆚 ዋትፎርድ ➡️ 4:30
ማን ዩናይትድ ከ ቶተንሃም ➡️ 4:30
ሳውዝሀምተን 🆚 ኖርዊች ሲቲ ➡️ 4:30
ዎልቭስ 🆚 ዌስትሀም ➡️ 4:30
ሊቭርፑል ከ ኤቨርተን ➡️ 5:15


⚽️ቅድመ ጨዋታ ትንታኔ | ማን ዩናይትድ ከ ቶተንሃም


✅ዛሬ ምሽት 4:30 በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማን ዩናይትድ ከ ቶተንሃም በኦልድ ትራፎርድ ይጫወታሉ።ከዚህ ጨዋታ ጋር በተያያዘ ያሉትን መረጃዎች እንመልከት

➡️የቡድን ዜና
✅ፖል ፖግባ ዛሬም በጉልበት ጉዳት ከሜዳ ውጪ ነው።

✅ስኮትላንዳዊው አማካይ ስኮት ማክቶሚናይ ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ዛሬ ከጉዳቱ አገግሟል።ኒማኒያ ማቲች ግን ከዛሬው ጨዋታ ውጪ ነው።

✅ኤሪክ ላሜላ እና ሚካኤል ቮርም በብሽሽት ጉዳት ከዛሬው ጨዋታ ውጪ ናቸው።ሁጎ ሎሪስ እና ቤን ዳቪስም በተመሳሳት በጨዋታው አይሰለፉም።

➡️የአሰልጣኝ አስተያየቶች

✅ኦሊ ጉናር ሶልሻየር - "ጆዜ ሞሪንሆ ጥሩ አቀባበል ይደረግለታል።ለክለቡም ሆነ ለደጋፊዎቹ ይሄ ክብር ነው።ያለጥርጥር እሱ የነበረበትን እና ዋንጫዎችን ያነሳበትን ጊዜ ያስታውሳሉ።

"ሀምሳ ጨዋታዎችን አድርጌያለሁ ነገር ግን መሆን ያለብን ቦታ አይደለም ያለነው።መሆን የምንፈልገውም በዚህ ደረጃ አይደለም ስለዚህ ማሻሻል አለብን።

✅ጆዜ ሞሪንሆ - "ትላልቅ ጨዋታዎችን ማድረግ እወዳለሁ።ከምርጥ ቡድኖች በተቃራኒ መጫወት ያስደስተኛል እናም ወሳኝ ነገር ነው።

"ወደ ኦልድ ትራፎርድ መመለስ ደስተኛ ወደ ነበርኩበት ቦታ መመለስ ማለት ነው።ይህንን ነው ማለት ምችለው።ከማን ዩናይትድ ደጋፊዎች ጋር ጠንካራ ግንኙነት አለኝ።"

➡️የጨዋታ ዕውነታዎች
➡️የእርስ በእርስ ግንኙነቶች
✅ቶተንሃም በማን ዩናይትድ 34 ጊዜ ተሸንፏል።በዚህም ቶተንሃምን የማን ዩናይትድ ያህል ያሸነፈ ክለብ የለም።

✅ቶተንሃም ኦልድ ትራፎርድ ላይ ባለፉት ተከታታይ አራት ጨዋታዎች ግብ ማስቆጠር አልቻለም።

➡️ማን ዩናይትድ
✅ዩናይትድ በሁሉም የውድድር አይነቶች ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች አልተሸነፈም (4ድል 4አቻ)

✅ማን ዩናይትድ ከ1988-89 በኋላ ዘንድሮ ደካማ አጀማመር ነው ያደረገው።በ14 ጨዋታዎች 18 ነጥብ ብቻ ነው የሰበሰበው።

✅ባለፉት 25 ጨዋታዎች 2ጊዜ ብቻ ነው ግብ ሳይቆጠርበት መውጣት የቻለው።

✅ማን ዩናይትዶች ዘንድሮ ካገኟቸው ስድስት የፍፁም ቅጣት ምቶች አራቱን አምክነዋል።

➡️ቶተንሃም

✅ጆዜ ሞሪንሆ ዛሬ ካሸነፉ ሶስት ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን እንደተሾሙ በማሸነፍ የመጀመሪያው የስፐርስ አሰልጣኝ ይሆናሉ።

✅ቶተንሃም በዘንድሮው አመት ከሜዳው ውጪ ባደረጋቸው ሰባት ጨዋታዎች አንድ ብቻ ነው ያሸነፈው።

✅ዴሊ ዓሊ ባለፉት ሁለት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሶስት ግቦች አስቆጥሯል።

✅ሀሪ ኬን ከማን ዩናይትድ ጋር በተጫወተባቸው አስር ጨዋታዎች ሁለት ግብ  ብቻ ነው ያስቆጠረው።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...