Wednesday, December 4, 2019

'ባለውለታን አለመርሳት ……'

'ባለውለታን አለመርሳት ……'


አልበርት ባይኖር ክርስቲያኖ ሮናልዶ እዚህ ደረጃ መድረሱ አጠራጣሪ ነው ።በአሁኑ ሰዓት አምስት ጊዜ ባሎንዶርን በማሳካት ከምንጊዜም ምርጥ ተጨዋቾች አንዱ የሆነው ክርስቲያኖ በአንድ ወቅት አንድ አልበት ስለሚባል ሰው አስደናቂ ታሪክ ተናገረ።

"ጓደኛዬን አልበርትን አሁን ላለሁበት ስኬት ማመስገን ይገባኛል።ታዳጊ እያለን አብረን እንጫወት ነበር።ከዛ አንድ ቀን የስፖርቲንግ ሊዝበን መልማዮች መጥተው አንድ ጨዋታ ላይ ብዙ ግብ የሚያስቆጠረውን ሰው ወደ አካዳሚው
እንደሚያስገቡ ተነገረን።ያንን ጨዋታ 3ለ0 አሸነፍን።እኔ የመጀመሪያውን ጎል አስቆጠርኩ ከዛ አልበርት በግንባሩ (ቴስታ) ሁለተኛውን ግብ አስቆጠረ።ሶስተኛው ጎል ግን ብዙዎችን አስደመመ።አልበርት ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኘ፡፡እኔ ከዙ ጀርባ እየሮጥኩ ነበር፡፡ከዛ ግብ ጠባቂውን አለፈው የቀረው ባዶ የነበረውን ግብ ማስቆጠር ነበር፡፡ያን ሰዓት እኔ አጠገቡ ደርሼ ነበር እና ባዶ የነበረውን ማስቆጠር ሚችለውን ኳስ ለኔ አቀበለኝ እና አስቆጠርኩት፡፡
ከዛ አካዳሚው እኔን ተቀበለኝ።ከጨዋታው በኋላ አልበርትን 'ለምን' ያንን እንዳደረገ ጠየኩት እሱም 'ምክንያቱም አንተ ከኔ የተሻልክ ነህ' አለኝ።"


ይህ ታሪክ ከተፈፀመ ከበርካታ አመታት በኋላ አንድ ጋዜጠኛ ወደ አልበርት ቤት አምርቶ ታሪኩ እውነት መሆኑን ጠየቀው እርሱም 'አዎን' ሲል መለሰ።ከዛም ከዛች ቀን ጀምሮ የእግር ኳስ ህይወቱ እንዳበቃ እና ስራ እንደሌለው ነገረው።

ጋዜጠኛው በመደነቅ " ስራ ከሌለህ ይሄን የመሰለ ውብ ቤት እንዚያን የመሰለ ቅንጡ መኪናዎች ከየት አመጣሃቸው።ቤተሰቦችህም ጥሩ ነው ያሉት በጣም
የሀብታም ኑሮ እኮ ነው የምትኖረው " ሲል ጠየቀው
አለበርትም መለሰ "ሁሉንም የሰጠኝ ክርስቲያኖ ነው"

1 comment:

  1. ደሰ ሲል ሁሌ ለሰው መልካም ነገር ስታደርግ እያው ያድረከው ነገር መልሶ ይጠብቃህል::

    ReplyDelete

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...