ሪያል ማድሪድ ከጆዜ ሞሪንሆ ጋር ንግግር ጀምሯል
አቅራቢ-አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ከማን ዩናይትድ ባሳለፍነው ሲዝን የተሰናበቱት ጆዜ ሞሪንሆ ስማቸው ከበርካታ ክለቦች ጋር እንዲሁም ከሀገራቸው ፖርቱጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር ከተያያዘ ዋል አደር ብሏል።
ዛሬ El Chiringuito ባወጣው መረጃ መሰረት በዚነዲን ዚዳን ስር ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ሪያል ማድሪድ የቀድሞውን አሰልጣኙን ጆዜ ሞሪንሆን ወደ በርናቢዮ ለመመለስ ጥረት ማድረግ ጀምሯል።
ማድሪድ ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አዳጊው ማዮካ 1ለ0 መሸነፉ ደግሞ ዚዳን ላይ ያለውን ተፅዕኖ ይበልጥ እንዲበረታ አድርጓል።
ሞሪንሆ በብዙ ውዝግብ ታጅቦ በነበረው የሎስብላንኮዎቹ ቆይታቸው ሶስት አመት የቆየ ሲሆን (2010-2013) እምብዛም ስኬታማ የሚባል ጊዜን አላሳለፉም ነበር።
No comments:
Post a Comment