Tuesday, October 15, 2019

የማክሰኞ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ  - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)

የሀገር ውስጥ ዜናዎች

ታሪክን የኋሊት
ዛሬ ጥቅምት 4 ነው።ይህንን ዕለት በርካታ ኢትዮጵያውያን የማንዘነጋው ነው።ከስምንት አመት በፊት 2004 ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ያለፈችበት ዕለት ነበር ፥ ከ31 አመት በኋላ።
በዚህ ጨዋታ ኢትዮጵያ ሱዳንን በአዳነ ግርማ እና ሳልሃዲን ሰኢድ ግቦች 2ለ0 መርታቷ አይረሴ ነበር።በጨዋታው አዲስ  ህንፃ ተቀይሮ ገብቶ የፈጠረው ተፅዕኖ እስከዛሬ በብዙዎቻችን ልብ ውስጥ የቀረ በጎ ትውስታ ነበር።

በወቅቱ ለነበሩት ሙሉ  ተጨዋቾች እና አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው እንዲሁም አጠቃላይ የአሰልጣኝ ክፍሉ ዛሬም እናመሰግናለን!



↳ሪችሞንድ አዶንጎ ብርቱካናማዎቹን ተቀላቀለ
ገና በለጋ ዕድሜው ወደ ስዊድኑ ጉተንበርግ አምርቶ የአንድ
ዓመት ቆይታ ካደረገ በኃላ በ2010 ወደ ሃገሩ ጋና በመመለስ ከበርኩም ቸልሲ ፣ አሚዱስ እና ሌበሪቲ
ፕሮፌሽናልስ ሶስት የተሳኩ ዓመታት ያሳለፈው አጥቂው
በዛምቢያው ብዩልድ ኮን የአንድ ዓመት ቆይታ ካደረገ በኃላ ነው በ2010 አጋማሽ ወልዋሎን የተቀላቀለው። በክለቡ
የ18 ወራት ቆይታ ካደረገ በኋላም ወደ ምስራቁ ክለብ
ተጉዟል።
ወደ ዝውውር መስኮቱ ዘግይተው የገቡት ድሬዳዋ
ከተማዎች ቀደም ብለው የአሰልጣኝ ስምዖን አባይ ውል
በማራዘም ተጫዋቾች እያስፈረሙ ሲገኙ ቡድኑን
ተቀላቅለው ከነበሩት መካከል ከዘካርያስ ቱጂ እና ፋሲል
አስማማው ጋር በስምምነት መለያየታቸው ታውቋል።
(Soccer  Ethiopia)


የውጭ ሀገር ዜናዎች


↳ትናንት በዩሮ 2020 ማጣሪያ ጨዋታ ዩክሬን ፖርቱጋልን አስተናግዳ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።በዚህ ጨዋታ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለፖርቱጋል አንዷን እና ብቸኛዋን ግብ በፍፁም ቅጣት ምት ያስቆጠረ ሲሆን በአጠቃላይ በእግር ኳስ ህይወቱም  700ኛ ግቡ ሆኖ ተመዝግቦለታል።
ያቆጠራቸውን ግቦች በክለብ ደረጃ ስንመለከት
⇛ስፖርቲንግ ሊዝበን 5⚽️
⇛ማን ዩናይትድ 118⚽️
⇛ሪያል ማድሪድ 450⚽️
⇛ጁቬንትስ 32 ⚽️
⇛ለፖርቱጋል ብሔራዊ ቡድን ደግሞ 95 ነው።
(Opta)




↳ትናንት በዩሮ ማጣሪያ እንግሊዝ ከሜዳዋ ውጪ ቡልጋሪያን 6ለ0 ያሸነፈች ሲሆን በዚህ ጨዋታ የቡልጋሪያ ደጋፊዎች ከፍተኛ የዘረኝነት ጥቃትን በእንግሊዝ ጥቁር ተጨዋቾች ላይ ሲሰነዝሩ ነበር።በጨዋታው ከደጋፊዎች አልፎ ውስጥ የነበሩ የቡልጋሪያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾችም ተሳታፊ መሆናቸው ብዙዎችን አሳዝኗል።
(Goal)





↳ስማቸው ከማን ዩናይትድ ጋር እየተያያዘ የሚገኘው የቀድሞው የጁቬንትስ አሰልጣኝ ማሲሚሊያኖ አሌግሪ ቀያይ ሰይጣኖቹን የሚቀላቀሉ ከሆነ ፓትሪስ ኤቭራ የአሰልጣኝ ቡድኑ ውስጥ እንዲካተትላቸው ይፈልጋሉ።
(Daily Mail)




↳የማን ዩናይትድ ባለቤት ከሆኑት ስድስቱ የግሌዘር ቤተሰቦች አንዱ የሆኑት ኬቨን ግሌዘር ከድርሻቸው ውስጥ 13% ሊሸጡት ነው።የግሌዘር ቤተሰቦች በኢድ ውድ ዋርድ እየተመሩ ማን ዩናይትድን የቁልቁለት ጉዞ አስይዘውታል ተብለው በብዛት ይተቻሉ።
(The Sun)




↳ማውሩዚዮ ሳሬ ጣሊያናዊውን ተከላካይ ኤመርሰን ፓልሜይሪ እና ፈረንሳዊውን አማካይ ንጎሎ ካንቴ ከቼልሲ ማዘዋወር ይፈልጋሉ።ሳሪ በጣሊያን ሴሪያ ከኢንተር ሚላን ጋር ክለባቸው ጁቬንትስ ትንቅንቅ ውስጥ መግባቱ ይታወቃል።
(Daily Express)




↳ኤሲ ሚላን በውሰት ቤስኪታሽ የሚገኘውን የአርሰናሉን አማካይ ሙሐመድ ኤልኒኒ የማዘዋወር ፍላጎት አለው።ግብፃዊው የ27 አመት አማካይ በኡናይ ኤምሬ አይፈለግም።
(Gazzetta - in Italian)




↳የቀድሞው የቶተንሃም አሰልጣኝ ሀሪ ሬድናፕ ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ ማን ዩናይትድ ለመሄድ ብሎ ቶተንሃምን ከለቀቀ ትልቅ ስህተት ነው ሚሆነው ብለዋል።ሬድናፕ አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ወደ ኦልድ ትራፎርድ ካቀና ስኬታማ ለመሆን በርካታ አመታት ይፈጁበታል ብለዋል፡፡
(Mirror)




↳ለብራዚል ብሔራዊ ቡድን ሲጫወት ጉዳት ያስተናገደው ኔይማር ለአራት ሳምንት ከሜዳ እንደሚርቅ ፓሪሰን ዤርመን ይፋ አድርጓል፡፡የ27 አመቱ የአለማችን ውድ ተጨዋች በጡንቻ መሸማቀቅ ምክንያት ነው ከሜዳ የሚርቀው።
(Mirror)




↳የጣሊያን ብሔራዊ ቡድንን ከወዲሁ ለዩሮ 2020 እንዲያልፍ ያደረገው ሮበርቶ ማንቺኒ እስከ 2022 ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የሚያቆየውን ኮንትራት ፈርሟል።ማንቺኒ እስከ 2020 የሚያቆይ ኮንትራት ነበር የነበረው።
(Mail)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...