የሀገር ውስጥ ዜናዎች
አዳማ ከተማ አጥቂ አስፈረመድሬዳዋ ከተማ በአሰልጣኝ መሠረት ማኔ እየተመራ ወደ
ፕሪምየር ሊግ ባደገበት የብሔራዊ ሊግ የማጠቃለያ
ውድድር ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ያጠናቀቀው ይህ
ተጫዋች ወልዲያ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም
ባለፈው የውድድር ዓመት ቤንች ማጂ ቡና
የተጫወተባቸው ክለቦች ሲሆኑ በመሐል እና የመስመር
አጥቂነት መጫወት ይችላል።
በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እየተመሩ ዝግጅታቸው በማድረግ
ላይ የሚገኙት አዳማዎች ሁለት የአቋም መለኪያ
ጨዋታዎች ከአንድ የባቱ እና ከአንድ የመተሐራ ቡድኖች
ጋር አድርገው በሰፊ ውጤቶች ያሸነፉ ሲሆን ከትናንት በስቲያ ደግሞ ቢሾፍቱ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2-0 አሸንፈዋል።
(Soccer Ethiopia)
የውጭ ሀገር ዜናዎች
የቀድሞው የፖርቶ ፥ ቼልሲ ፥ ኢንተር ሚላን ፥ ሪያል ማድሪድ እና ማን ዩናይትድ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ እሳቸው ኳስ መመልከት ከጀመሩ አንስቶ ብራዚላዊውን አጥቂ ሮናልዶ የሚያህል ተጨዋች እንዳላዩ ተናግረዋል።ጆዜ ኤልፌኔሚኖ ከሊዮኔል ሜሲም ሆነ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ የላቀ ተጨዋች ነው ብለዋል፡፡
(Goal)
የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ስካሎኒ ሜሲ በቀጣይ ወር የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን እንደሚቀላቀል ተናግረዋል።አርጀንቲናዊው ኮከብ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጉዳት እየተጠቃ መሆኑ ይታወቃል።
(Goal)
(Sport1, via Sunday Mirror)
በሬንጀርስ አስደናቂ ጊዜን እያሳለፈ ያለው የቀድሞው የሊቨርፑል ሌጀንድ አሰልጣኝ ስቴቨን ዤራርድ በቀጣዩ አመት ዤርመን ዴፎን የአሰልጣኝነት ቡድኑ ውስጥ ማካተት ይፈልጋል።
(Daily Record)
ቀውስ ላይ የሚገኘው ማን ዩናይትድ በጥር ወር የዝውውር መስኮት የዌስት ሃሙን እንግሊዛዊ አማካይ ዴክላን ሪስ ለማዘዋወር £70ሚ. ድረስ ሊያወጣ ይችላል።ኦሊ ጉናር ሶልሻየር የ20 አመቱን አማካይ በጥብቅ ይፈልገዋል።
(Sunday Mirror)
የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ሊያስፈርማቸው ካቀዳቸው ተጨዋቾች ውስጥ ሁለት እንግሊዛውያን ይገኛሉ።እነዚህም የቶተንሃሙ የ26 አመት አጥቂ ሀሪ ኬን እና የ21 አመቱ ማርከስ ራሽፎርድ ናቸው።
(Mundo Deportivo - in Spanish)
አርሰናል ለፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ አዲስ ኮንትራት አቅርቧል።የ30 አመቱ አጥቂ በኤምሬትስ ለሁለት አመት የሚያቆይ ኮንትራት ያለው ሲሆን መድፈኞቹ እስከ 2023 የሚያቆይ ኮንትራት ነው ያቀረቡለት።
ኦባማያንግ ከዶርትመንድ አርሰናልን ከተቀላቀለ አንስቶ 75 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 49 ግቦች አስቆጥሯል።
(La Gazzetta dello Sport)
ባርሴሎና ኢቫን ራኪቲችን በጥር ወር የዝውውር መስኮት መሸጥ ይፈልጋል።የ31 አመቱ ክሮሺያዊ በዘንድሮው አመት አንድ ጊዜ ብቻ በቋሚነት መሰለፍ የቻለ ሲሆን በኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ስርም ደስተኛ አይደለም።
(AS)
ማንችስተር ሲቲ ክረምት ላይ ውሉ ለሚያልቀው ሁለገቡ ተጨዋች ፈርናንዲንሆ አዲስ ኮንትራት ሊያቀርብለት ነው።ውሃ ሰማያዊዎቹ ለ34 አመቱ ብራዚላዊ የአንድ አመት ተጨማሪ ውል ነው ያሰናዱለት።
(The Sun)
No comments:
Post a Comment