አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
"ኢሊ ጉናር ሶልሻየር የዓለማችን ምርጥ ተጨዋቾች አሁንም መጫወት የሚፈልጉበት ክለብ ነው ማንቸስተር ዩናይትድ" ሲል ተናግሯል።ኦሌ በጋዜጣዊ መግለጫው ማን ዩናይትድ ኮከብ ተጨዋቾችን የማስፈረም ችግር እንደማይገጥመው ተናግሯል።"ማን ዩናይትድ የዓለማችን ትልቁ እና ምርጡ ክለብ ነው።" ሲልም አክሏል።
(Goal)
የዎልፍስ በርጉ ግብ ጠባቂ ኮይን ካስትልስ በጀርመኑ ክለብ እስከ 2024 የሚያቆየውን ኮንትራት ፈርሟል።በዘንድሮው አመት በቡንደስ ሊጋው አስደናቂ ግስጋሴን እያደረገ ባለው ዎልፍስበርግ ውስፍ የካስትልስ ሚና ከፍተኛ ነው።
(Official)
ስካይ ስፖርትስ እንደዘገበው ትናንት ምሽት በሻምፒዮንስ ሊግ ሊቨርፑል ከሜዳው ውጪ ሬድቡክ ሳልዝቡርግን በገጠመበት ጨዋታ ማን ዩናይትድ ወደ ኦስትሪያ ኤርሊንግ ሀላንድን እንደመለከቱ መልማዮችን ልኮ ነበር።
በትናንቱ ጨዋታ የነበሩት ከማን ዩናይትድ መልማዩ ማርሴል ቦውት በመሪነት ሲሆን ሌሎች የ39 ክለብ መልማዮችም ነበሩ።
(Sky Sports)
ትናንት ከሁለት ዓመታት ገደማ ቆይታ በኋላ ከናፖሊ የተሰናበቱት ጣሊያናዊው አንጋፋ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ከወዲሁ ስማቸው ከበርካታ ክለቦች ጋር በመያያዝ ላይ ይገኛል።ከነዚህ ክለቦች መሀከል ኡናይ ኤምሬን ያሰናበተው አርሰናል አንዱ ነው።
(Goal)
ማን ዩናይትድ ፖል ፖግባን በቀጣዩ ክረምት ለመሸጥ ወስኗል።
ቀያይ ሰይጣኖቹ በባርሴሎና ፥ ሪያል ማድሪድ እና ጁቬንትስ የሚፈለገውን ፈረንሳዊውን የ26 አማካይ ፖል ፖግባ በአመቱ መጨረሻ ለመሸጥ ወስነዋል።በምትኩ የአያክሱ አማካይ ቫን ደ ቢክ ወይም የአትሌቲኮ ማድሪዱን ሳውል ኒጉዌዝ ወደ ኦልድ ትራፎርድ ለማስኮብለል ወጥነዋል።
(Daily Mail)
ጁቬንትስ ከቼልሲ ጋር በብራዚላዊው የክንፍ አጥቂ ዊልያን ጉዳይ መነጋገር ጀምሯል።በአመቱ መጨረሻ ውሉ የሚጠናቀቀውን ተጨዋች አሮጊቷ የጥር ወር የዝውውር መስኮት ነው ማዘዋወር የምትፈልገው።
ፍራንክ ላምፓርድ ግን ዊልያን በስታንፎርድ ብሪጅ እንዲቆይ ይፈልጋል።
(the Daily Express)
ትናንት ምሽት ካርሎ አንቾሎቲን ያሰናበተው ናፖሊ አንጋፋውን የቀድሞ የኤሲ ሚላን ሌጀንድ ጄናሮ ጋቱሶ በአሰልጣኝነት ሊሾም ነው።ጋቱሶ በዚህ አመት ከሚላን አሰልጣኝነቱ መሰናበቱ ይታወሳል።
(Sky Sports Italy)
ተጨዋቾችን የማስፈረም እገዳው የተነሳለት ቼልሲ የአጥቂ መስመር ተጨዋቾችን ለማስፈረም እየሰራ ነው።
ቼልሲ በዘንድሮው አመት በሻምፒዮንስ ሊግ 11 እንዲሁም በፕሪሚየር ሊጉ 31 ግቦችን ተቃራኒ ክለብ ላይ ያስቆጠረ ቢሆንም ፍራንክ ላምፓርድ በተሻለ መልኩ የአጥቂ መስመሩ እንዲጠናከር ይፈልጋል።
(Goal)
ኢንተር ሚላን ሁለት ተጨዋቾችን ከባርሴሎና ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።እነዚህ ተጨዋቾች ዘንድሮ በቫልቬርዴ በቂ የመሰለፍ ዕድል ያልተሰጣቸው አርትሮ ቪዳል እና ኢቫን ራኪቲች ናቸው።
(Sky Sports Italy)
No comments:
Post a Comment