Thursday, December 12, 2019

የሐሙስ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

                      አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ጆዜ ሞሪንሆ የናፖሊው ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ ወደ ቶተንሃም እንዲመጣላቸው ይፈልጋሉ።
ጆዜ ሞሪንሆ ከመጡ አንስቶ ቶተንሃም በተቃራኒ ቡድኖች ላይ በርካታ ግቦችን ያስቆጠረ ቢሆንም በዛው ልክ ግቦች ሲቆጠሩበት ታዝበናል።በዚህም ምክንያት ነው ፖርቱጋላዊው አሰልጣኝ የኋላ ክፍላቸውን ለማጠናከር ያሰቡት።


(Calciomercato)

ስሙ በስፋት ከባርሴሎና ጋር ሲያያዝ የቆየው ዊልያን በቼልሲ ቤት ለመቆየት በአዲስ ኮንትራት ጉዳይ እየተነጋገረ መሆኑን ተናግሯል።ለስድስት አመት ከግማሽ በምዕራብ ለንደኑ ክለብ የቆየው ብራዚላዊ ኢንተርናሽናል ምናልባትም ይህ ሲዝን የመጨረሻው እንዳይሆን ሲባል ቆይቷል።ሆኖም አሁን ዊልያን ከክለቡ ጋር በአዲስ ኮንትራት ጉዳይ ንግግር ላይ መሆኑን አሳውቋል።
(Goal)



ጁቬንትስ ለጎንዛሎ ሂጎይን አዲስ ኮንትራት ሊያቅርብለት ነው።አርጀንቲናዊው የ32 አመት አጥቂ ስሙ ከሀገሩ ክለብ ሪቨር ፕሌት ጋር እየተያያዘ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በአሮጊቷ እስከ 2021 የሚያቆይ ኮንትራት ነው ያለው።
(Calcio Mercato)




አትሌቲኮ ማድሪድ ሳውል ኒጊዌዝን የሚሸጠው £128ሚ. እንደሆነ ለማን ዩናይትድ አሳውቋል።ቀያይ ሰይጣኖቹ የፖል ፖግባን በክለቡ መቆየት እርግጠኛ ስላልሆኑ ስፔናዊውን አማካይ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ለማዘዋወር የተቻላቸውን ጥረት ያደርጋሉ።
(Mundo Deportivo)



ኤቨርተን ከ38 አመቱ ስዊድናዊ ኢንተርናሽናል ዝላታን ኢብራሒሞቭች ወኪል ሚኖ ራዮላ ጋር ንግግር መጀመሩ ታውቋል።በጊዜያዊነት በቀድሞው ተጨዋቹ ደንከን ፈርጉሰን እየተመራ ያለው ኤቨርተን የቀድሞውን የማን ዩናይትድ ተጨዋች በጥብቅ ይፈልገዋል።ከወደ ጣሊያንም ኤሲ ሚላን ዝላታንን ይፈልገዋል።
(Arena Napoli, via Sport Witness)




ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከቶተንሃም የተሰናበቱትን እና በብዙ ክለቦች የሚፈለጉትን ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆን በአሰልጣኝነት ለመቅጠር እየሰራ ይገኛል።በአሁኑ ሰዓት የጀርመኑን ክለብ የያዙት ሉሲየን ፋቭረ በሲግናል ኢዱና ፓርል እምብዛም የሚቆዩ አይመስልም።
(Telegraph)



አርሰናል ካርሎ አንቾሎቲን የኤምሬ ተተኪ አድርጎ የመቅጠር ፍላጎት የለውም።በሳምንቱ አጋማሽ ከናፖሊ የተሰናበቱት ካርሊቶ ስማቸው በስፋት ከመድፈኞቹ ጋር ሲያያዝ መቆየቱ ይታወሳል።
(ESPN)



የቀድሞው የአርሰናል ተጨዋች ማይክል አርቴታ ቀጣዩ የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ሊሆን እንደሚችል በሰፊው እየተዘገበ ነው።በአሁኑ ሰዓት የፔፕ ጋርዲዮላ ምክትል ሆኖ እየሰራ ያለው አርቴታ ወደ አርሰናል የመሄድ ፍላጎት ያለው ሲሆን በኤምሬትስ ምን ያህል ቆይታ ሊሰጠው እንደሚገባ ግን መደራደር ይፈልጋል።
(The Sun)




ቼልሲ የአጥቂ ስፍራውን ለማጠናከር የክሪስታል ፓላሱን ዊልፍሬድ ዘሃ ለማስፈረም በመንቀሳቀስ ላይ ነው።ሰማያዊዎቹ ኮዲቫራዊውን አጥቂ ለማዘዋወር የተጠየቁት £80ሚ. ሲሆን ክሪስታል ፓላስ ከዚህ በታች እንደማይሸጥ አሳውቋቸዋል።ቼልሲ ከሁለት ሲዝን እገዳ በኋላ ተጨዋቾችን እንዲያስፈርም በአለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (ካስ) እንደተፈቀደለት ይታወሳል።
(Evening Standard)








✅ትናንት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች መጠናቀቃቸው ይታወቃል።ኮከብ ግብ አግቢዎቹ የሚከተሉት ናቸው

 1.ሮበርት ሌዋንዶልስኪ ➡️ 10

2.ኤርሊንግ ሀላንድ ➡️ 8

3.ሀሪ ኬን ➡️ 6

4.ኪልያን ምባፔ ➡️ 5

= ራሂም ስተርሊንግ ➡️ 5

=ሂውንግ ሚን ሰን ➡️ 5

=ድረስ መርቲንስ ➡️ 5

=ሜምፊስ ዴፓይ ➡️ 5

=ማውሮ ኢካርዲ ➡️ 5

=ላውታሮ ማርቲኔዝ ➡️ 5
(Bleacher Report)





No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...