Thursday, December 12, 2019

የዕለተ አርብ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                     አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና  ልጅ)

ማን ዩናይትድ የቦሩሲያ ዶርትሙንዱን የ19  አመት እንግሊዛዊ የክንፍ አጥቂ ጄደን ሳንቾ በቀጣዩ ወር በሚከፈተው የጥር ወር የዝውውር መስኮት ወደ ኦልድ ትራፎርድ እንደሚያመጣ ተማምኗል።ቀያይ ሰይጣኖቹ በተጨማሪም ዴንማርካዊውን የቶተንሃም አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰንንም የማዘዋወር ዕቅዱ አላቸው።
(Mirror)



ፔፕ ጋርዲዮላ ኮንትራቱን በማቋረጥ በአመቱ መጨረሻ ማንቸስተር ሲቲን ሊለቅ ይችላል፡፡ውሃ ሰማያዊዎቹን ከተቀላቀለ አንስቶ ሁለት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ያሳካው ፔፕ በዘንድሮው አመት  ግን ደካማ ጊዜ ነው በኢቲሀድ እያሳለፈ ያለው።
(Mail)



ዌስት ሀም የቀድሞውን የቶተንሃም አሰልጣኝ ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ የማንዌል ፔሌግሬኒ ምትክ አድርጎ መሾም ይፈልጋል።ካክተሳካ ደግሞ እንደ ሁለተኛ አማራጭ የቀድሞው አሰልጣኛቸውን ሀሪ ሬድናፕን አቅደዋል።
(Star)



በጊዜያዊነት በቀድሞው ተጨዋቹ ደንከን ፈርጉሰን እየሰለጠነ የሚገኘው ኤቨርተን ከአርሰናል በቅርቡ የተሰናበቱትን ኡናይ ኤምሬን በአሰልጣኝነት የመሾም ፍላጎት አለው።ስፔናዊው አሰልጣኝ ግን በዚህ ፍጥነት ወደ ሊጉ የመመለስ ፍላጎት የላቸውም።
(ESPN)



ዘንድሮው በኦስትሪያው ክለብ ሬድ ቡል ሳልዝበርግ አስደናቂ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው ኤርሊንግ ሀላንድ ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ እና ራ.ቢ. ሌብዚሽ የዝውውር ጥያቄ እንደቀረበለት ታውቋል።ሆኖው ኖርዌያዊው የ19 አመት አጥቂ ቀጣይ ማረፊያውን ለመወሰን የማንቸስተር ዩናይትድን እና ጁቬንትስን ጥያቄ በመጠበቅ ላይ ይገኛል።
(Guardian)



ክሪስታል ፓላስ ኮዲቫራዊውን አጥቂ ዊልፍሬድ ዘሃ ለመሸጥ ከቼልሲ £80ሚ. ይፈልጋል።የሁለት ሲዝን እገዳው በአለም ዓቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (ካስ) የተነሳለት ቼልሲ ተጨዋቹን አጥብቆ ይፈልገዋል።
(Evening Standard)




ናፖሊ ኡራጋዊውን የአርሰናል አማካይ ሉካስ ቶሬራ በውሰት ለመውሰድ ጥያቄ አቅርቧል።የኔፕልሱ ክለብ በውሰት የማይሆን ከሆነ የ23 አመቱን አማካይ በ£21ሚ. በቋሚነት ማዘዋወር ይፈልጋል።
(Il Mattino - in Italian)




በፓሪሰን ዤርመን  እምብዛም ስኬታማ ያልሆነው የ27 አመቱ ብራዚላዊ ኢንተርናሽናል ኔይማር በፓሪሱ ክለብ ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል።የዓለማችን የዝውውር ሪከርድ በሆነ ዋጋ ፔዤ የተቀላቀለው ኔይማር ስሙ በስፋት  ከቀድሞው ክለቡ ባርሴሎና  እና ከሌሎች ሐያላን የአውሮፓ ክለቦች ጋር ይያያዛል።
(AS)



በአሁኑ ሰዓት በቻይናው ክለብ ሻንጋይ ሊውንግስ የሚገኘው ቤልጄሚያዊውን አማካይ ማርዋን ፌይላኒን ለማዘዋወር ቶተንሃም ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ጆዜ ሞሪንሆ በማን ዩናይትድ ሳሉ ከተጨዋቹ ጋር አንድ ላይ መስራታቸው ይታወሳል።
(Eleven Sports via Evening Standard)



በቼልሲ ያለው ኮንትራት በዓመቱ መጨረሻ የሚያበቃው ስፔናዊው የ32 አመት አጥቂ ፔድሮ ሮድሪጌዝ  በድጋሚ በባርሴሎና የመጫወት ዕድሉን ሊያገኝ ይችላል።
(Sport)




ማንቸስተር ዩናይትድ ፈረንሳዊውን የ26 አመት አማካይ ፖል ፖግባ በጥር የዝውውር መስኮት የመሸጥ ፍላጎት የለውም።
(Goal)

2 comments:

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...