ነገ ምሽት የዓለማችን ትልቁ የክለቦች ፍጥጫ የሆነው ኤልክላሲኮ ኑ ካምፕ ላይ ይደረጋል።አርጀንቲናዊው ጥበበኛ ሊዮኔል ሜሲም ብዙ ጥያቄዎችን ተጠይቆ ምላሽ ሰጥቷል።ስለ ሀዛርድ እና ሮናልዶ ፥ ተቀያሪ ስለመሆን እና ለምን በርናቢዮ ላይ መጫወት ለባርሴሎና እንደሚቀለው ከጥያቄዎቹ ያብራራበት በጥቂቱ ናቸው።
ለምን ለባርሳ በርናቢዮ ላይ መጫወት እንደሚሻለው ሲያብራራ " በርናቢዮ ላይ ስንጫወት ብዙ ክፍት የሆኑ የሜዳ ክፍሎች ይኖራሉ።እነሱ [ማድሪድ[ እኛን ማጥቃት አለባቸው ፥ በሜዳቸው ስለሆነ እና ደጋፊዎቻቸውም ያንን ስለሚጠብቁ።
"ካፕም ኑ ላይ ግን የበርናቢዮውን በተቃራኒ ነው።በመጠኑ ወደ ኋላ አፈግፍገው ነው የሚጫወቱት ፥ በዚህ በጋራ ተከላክለው ከፊት ፈጣን ተጨዋቾች ስላሏቸው በካውንተር አታክ ያጠቃሉ።
"በርናቢዮ ላይ ሁለታችንም 90 ደቂቃውን እኩል ነው የምንጫወተው።ካምፕ ኑ ላይ ግን የተቆላለፈ እና ከባድ ጨዋታ ነው ሚሆነው።" ብሏል።
ስለ ሮናልዶ እና ሀዛርድ ደግሞ "ሀዛርድ ትልቅ ተጨዋች ቢሆንም ሮናልዶን መተካት ግን እጅግ በጣም ከባድ ነው።" ብሏል።
ሁለቱ የስፔን ሀያላን ክለቦች በነጥብ እኩል ሆነው ነገ ካምፕ ኑ ላይ ምሽት 4 ሰዓት ይፋለማሉ።
No comments:
Post a Comment