Tuesday, December 17, 2019

የዕለተ ረቡዕ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                       አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ማን ዩናይትድ ፈረንሳዊውን አማካይ ፖል ፖግባ በጥር ወር የዝውውር መስኮት የመሸጥ ፍላጎት የለውም።ለረዥም ጊዜ ከሜዳ የራቀው የ26 አመት አማካይ ከክለቡ መወጣት እንደሚፈልግ በተደጋጋሚ ተነግሯል።
(Mail)




ማን ዩናይትዶች ኖርዌያዊውን የ19 አመት አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ከክለቡ ሬድ ቡል ሳልዝቡርግ በ£76ሚ. እንደሚያዘዋውሩ ተማምነዋል።ቀያይ ሰይጣኖቹ ተጨዋቹን ካስፈረሙ በኋላ እስከ አመቱ መጨረሻ እዛው ሳልዝቡርግ በውሰት እንዲቆይም ነው የሚፈልጉት።
(Sun)




ኤቨርተን ጣሊያናዊውን አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ለመሾም እየሞከረ ሲሆን አሁን ጥሩ አጀማመር እያደረገ ያለው ደንከን ፈርጉሰን ከአንቾሎቲ ጋር በጋራ ኮቺንግ ስታፍ ውስጥ ሆኖ  እንዲሰራ ይፈልጋሉ፡
(Telegraph)





የ34 አመቱ ፖርቱጋላዊ ኢንተርናሽናል ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወኪል የሆነው ጆርጌ ሜንዴዝ ሮናልዶ የእግር ኳስ ህይወቱን በጁቬንትስ ሊጨርስ ይችላል ሲል ተናግሯል።ሜንዴዝ ፖርቱጋላዊው ኮከብ ያለፉትን ሁለት አመታት ባሎንዶር ሊያሸንፍ ይገባ ነበርም ብሏል።
(Sky Sports, via Goal)





ሊዮኔል ሜሲ ኤልክላሲኮን አስመልክቶ ሰፋ ያለ አስተያየት ሰጥቷል



ዛሬ ምሽት የዓለማችን ትልቁ የክለቦች ፍጥጫ የሆነው ኤልክላሲኮ ኑ ካምፕ ላይ ይደረጋል።አርጀንቲናዊው ጥበበኛ ሊዮኔል ሜሲም ብዙ ጥያቄዎችን ተጠይቆ  ምላሽ ሰጥቷል።ስለ ሀዛርድ እና ሮናልዶ ፥ ተቀያሪ ስለመሆን እና ለምን በርናቢዮ ላይ መጫወት ለባርሴሎና እንደሚቀለው ከጥያቄዎቹ ያብራራበት በጥቂቱ ናቸው።


ለምን ለባርሳ በርናቢዮ ላይ መጫወት እንደሚሻለው ሲያብራራ " በርናቢዮ ላይ ስንጫወት ብዙ ክፍት የሆኑ የሜዳ ክፍሎች ይኖራሉ።እነሱ [ማድሪድ[ እኛን ማጥቃት አለባቸው ፥ በሜዳቸው ስለሆነ እና ደጋፊዎቻቸውም ያንን ስለሚጠብቁ።


"ካፕም ኑ ላይ ግን የበርናቢዮውን በተቃራኒ ነው።በመጠኑ ወደ ኋላ አፈግፍገው ነው የሚጫወቱት ፥ በዚህ በጋራ ተከላክለው ከፊት ፈጣን ተጨዋቾች ስላሏቸው በካውንተር አታክ ያጠቃሉ።

"በርናቢዮ ላይ ሁለታችንም 90 ደቂቃውን እኩል ነው የምንጫወተው።ካምፕ ኑ ላይ ግን የተቆላለፈ እና ከባድ ጨዋታ ነው ሚሆነው።" ብሏል።



ስለ ሮናልዶ እና ሀዛርድ ደግሞ "ሀዛርድ ትልቅ ተጨዋች ቢሆንም ሮናልዶን መተካት ግን እጅግ በጣም ከባድ ነው።" ብሏል።



ሁለቱ የስፔን ሀያላን ክለቦች በነጥብ እኩል ሆነው ዛሬ ካምፕ ኑ ላይ ምሽት 4 ሰዓት ይፋለማሉ።
(Marca)




ሁለቱ የማንችስተር ከተማ ክለቦች ዩናይትድ እና ሲቲ የባርሴሎናውን የ16 አመት ታዳጊ የግራ መስመር ተከላካይ ሁዋን ላሪየስ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ፉክክር ውስጥ ገብተዋል፡፡
(Record)




ሪያል ቤቲስ በውሰት ቶተንሃም ያለውን ጆቫኒ ሌ ሶልሶን ለስፐርስ በቋሚነት የመሸጥ ፍላጎት አለው።አርጀንቲናዊው የ23 አመት አማካይ በጆዜ ሞሪንሆ ያለው ቦታ በውል አልታወቀም።
(Estadio Deportivo - in Spanish)




ባርሴሎና የ28 አመቱን ፈረንሳዊ አማካይ ንጎሎ ካንቴ ከቼልሲ የማዘዋወር ፍላጎት የለውም።
(Mundo Deportivo - in Spanish)




የፕሪሚየር ሊጎቹ ክለቦች ሊቨርፑል ፥ ማንችስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ ጀርመናዊውን የክንፍ አጥቂ ካይ ሀቬርት ለማዘዋወር ከፍተኛ ፉክክር ውስጥ ናቸው።የ20 አመቱ ተጨዋች ግን እዛው ባየርን ሊቨርኩሰን መቆየት ነው የሚፈልገው።
 (Sky Sports)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...