ሊቨርፑል ታኩሚ ሚናሚኖን አስፈረመ
ሊቨርፑል የሬድ ቡል ሳልዝቡርጉን አማካይ ታኩሚ ሚናሚኖ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።
ጃፓናዊው ኢንተርናሽናል ቀያዮቹን የሚቀላቀለው ከአስር ቀን በኋላ በፈረንጆቹ አዲስ አመት ሲሆን በአንፊልድ የአራት አመት ተኩል ኮንትራትም ፈርሟል።
ሚናሚኖ ከዝውውሩ በኋላ "የሊቨርፑል ተጨዋች መሆን ትልቁ ህልሜ ነበር " ብሏል።
የ24 አመቱ አማካይ 18 ቁጥር መለያም የሚለብስ ይሆናል።
No comments:
Post a Comment