አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
አርሰናል ማንችስተር ሲቲ ለሚኬል አርቴታ ውል ማፍረሻ የጠየቀውን £1ሚ. ለመክፈል ከስምምነት ላይ ደርሷል።በሲቲ ቤት የፔፕ ጋርዲዮላ አማካሪ ሆኖ ሲሰራ የነበረው አርቴታ በተጨዋችነት ወደ አገለገለበት ክለብ ወደ አርሰናል በነገው ዕለት አሰልጣኝ መሆኑ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
(Mail)
ካርሎ አንቾሎቲ ኤቨርተንን ለማስፈረም በመርህ ደረጃ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።የ60 አመቱ ጣሊያናዊ አሰልጣኝ የመርሲሳይዱ ክለብ አሰልጣኝ መሆናቸው ይፋ ሆኖ ሰኞ ስራ እንደሚጀምሩ የተገለፀ ሲሆን በአመት £11.5ሚ. የሚከፈላቸውም ይሆናል።
(Mirror)
ቶተንሃም ለጆዜ ሞሪንሆ በጥር ወር የዝውውር መስኮት የፈለጉትን ተጨዋች እንዲያዘዋወሩ በጀት ለማቅረብ ቃል ገብቶላቸዋል።ፖርቱጋላዊው አሰልጣኝ ግን በዚህ የዝውውር መስኮት ታላላቅ ተጨዋቾችን የማዘዋወር ዕቅዱ የላቸውም።የዌስት ብሮሙን ተከላካይ ናታን ፈርጉሰን እና የኖርዊች ሲቲውን የግራ መስመር ተከላካይ ማክስ አሮንስ ማምጣት ብቻ ነው ጆዜ ሚፈልጉት።
(Mail)
የቶተንሃሙ ሊቀ መንበር ዳኒ ሌቪ ዴንማርካዊውን አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን በእንግሊዝ ላሉ ታላላቅ ክለቦች ቢሸጡት እነደማያስጨንቃቸው ተናግረዋል።
(Evening Standard)
ሊቨርፑል የሬድ ቡል ሳልዝቡርጉን አማካይ ታኩሚ ሚናሚኖ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።
ጃፓናዊው ኢንተርናሽናል ቀያዮቹን የሚቀላቀለው ከአስር ቀን በኋላ በፈረንጆቹ አዲስ አመት ሲሆን በአንፊልድ የአራት አመት ተኩል ኮንትራትም ፈርሟል።
ሚናሚኖ ከዝውውሩ በኋላ "የሊቨርፑል ተጨዋች መሆን ትልቁ ህልሜ ነበር " ብሏል።
የ24 አመቱ አማካይ 18 ቁጥር መለያም የሚለብስ ይሆናል።
(Liverpool fc)
ፓሪሰን ዤርመን በማንችሰተር ሲቲ ዘንድሮ እምብዛም ስኬታማ ያልሆነውን ፔፕ ጋርዲዮላን የቶማስ ቱሀል ተተኪ አድርገው በአሰልጣኝነት የመሾም ፍላጎት አላቸው።
(Le 10 Sport via Daily Mail)
ከጉዳት ጋር እየታገለ ያለው የ23 አመቱ ጀርመናዊ ለሮይ ሳኔ ማንችስተር ሲቲን ለቆ ወደ ሀገሩ ክለብ ባየርን ሙኒክ መሄድ ይፈልጋል።ሳኔ ወደ ባቫሪያው ክለብ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ነው መሄድ የሚፈልገው።
(Bild via Mirror)
የባርሴሎናው የቀኝ መስመር ተከላካይ ኔልሰን ሴሜዶ ትናንት ከኤልክላሲኮ በፊት ቤቱ ተዘርፏል።ተጨዋቹ ትናንት በቋሚነት መሰለፉ ይታወሳል።
(Cadena SER via Marca)
ሊቨርፑል ፥ ቼልሲ እና ቶተንሃም የ20 አመቱን ናይጄሪያዊ የሊል አጥቂ ቪክቶር ኦሲሜንህ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።
(Sky Sports)

No comments:
Post a Comment