Thursday, December 19, 2019

የዕለተ አርብ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                       አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)

የ31 አመቱ ጀርመናዊ የአርሰናል አማካይ ሜሱት ኦዚል ወደ ቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለስድስት ወር በውሰት ሊዘዋወር ነው፡፡
(Fotomac, via Football.London)





የዩናይትድ ተጨዋቾችን እና አመራሮች ፖግባ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ኦልድ ትራፎርድን እንደሚሰናበት ተማምነዋል።ፈረንሳዊው የ26 አመት አማካይ በጁቬንትስ ፥ ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና በዋናነት ይፈለጋል።
(Mirror)




ካርሎ አንቾሎቲ ኤቨርተንን የሚቀላቀሉ ከሆነ የመጀመሪያ ዝውውራቸው የሚሆነው የቀድሞው የማን ዩናይትድ ግዙፉ አጥቂ  ዝላታን ኢብራሂሞቪችን ነው።ስዊድናዊው የ38 አመት አጥቂ ከአሜሪካው ክለብ ጋር ያለው ኮንትራት ጥር ላይ የሚያልቅ ሲሆን ከዛ በኋላ ነፃ ተጨዋች ይሆናል።
(Calcio Mercato)




በርካታ ሐያላን ክለቦች በተለይ ከእንግሊዝ የሪያል ማድሪዱን የ19 አመት ብራዚላዊ ዊንገር ቪኒሺየስ ጁኒየር በጥር ወር የዝውውር መስኮት የማዘዋወር ፍላጎት ያላቸው ሲሆን ቼልሲ ደግሞ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ነው።
(El Desmarque, via Star)





ሁለቱ የማንችስተር ከተማ ክለቦች ዩናይትድ እና ሲቲ የ20 አመቱን ጀርመናዊ የባየርን ሊቨርኩሰን አማካይ ካይ ሀቨርት ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል፡፡
(Manchester Evening News)





ጋቦናዊው የ30 አመት ኢንተርናሽናል ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ በአርሰናል ለመቆየት ከሚፈልጉ ተጨዋቾች ውስጥ ነው።ኦባማያንግ ምንም ያህል ብዙ ፈላጊዎች ቢኖሩትም በመድፈኞቹ ቤት ደስተኛ ነው።
(Independent)





የቶተንሃሙ ፕሬዝደንት ዳኒ ሌቪ በቅርቡ በአንድ ቢሊየን ፓውንድ የጨረሱትን ስቴዲየም ስያሜ ሊያከራዩት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ስፐርስ ከስቴዲየሙ ስያሜ ሪከርድ የሆነ £25ሚ.  በየዓመቱ እንደሚያገኝ ይጠበቃል፡፡
(Telegraph)





ማንችስተር ዩናይትድ ኖርዌያዊውን የሬድ ቡል ሳልዝቡርግ አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ ማስፈረም ከፈለገ ለወኪሉ ሚኖ ራዮላ £12ሚ. መክፈል አለበት ተብሏል።ራዮላ የፖግባም ወኪል መሆኑ ይታወቃል።
(Sun)





ብራዚላዊው የቶተንሃም አማካይ ሉካስ ሞራ 2012 ላይ ወደ ፓሪሰን ዤርመን ከመዘዋወሩ በፊት ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ሊሄድ እንደነበር እና በአንዳንድ ጉዳዮች አለ መሳካቱን ይፋ አድርጓል።
(ESPN Brasil, via Mirror)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...