Monday, December 16, 2019

የዕለተ ማክሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)

ሊዮኔል ሜሲ ለስድስተኛ ጊዜ ፒቺቺን አሸንፏል
ሊዮኔል ሜሲ ለስድስተኛ ጊዜ ፒቺቺን አሸንፏል።
በ2018/19 የውድድር ዘመን 36 የላሊጋ ግቦችን ማስቆጠር የቻለው አርጀንቲናዊው ጥበበኛ ሊዮኔል ሜሲ ትናንት የዓመቱ ምርጡ የላሊጋው ተጨዋች ተብሎ ፒቺቺን አሸንፏል።
[Marca]



ሚኬል አርቴታ ወደ አርሰናል በአሰልጣኝነት ሊሾም ከጫፍ ደርሷል

ኡናይ ኤምሬን አሰናብቶ በጊዜያዊነት በፍሬዲ ሊዩምበርግ እየሰለጠነ የሚገኘው አርሰናል የቀድሞው ተጨዋቹን ሚኬል አርቴታን በዋና አሰልጣኝነት ሊሾም ነው።በአሁኑ ሰዓት ከማን ሲቲ ቤት ከጋርዲዮላ ጋር እየሰራ ያለው አርቴታ ስሙ ከአርሰናል ጋር ሲያያዝ የሰነበተ ቢሆንም ትናንት የአርሰናል አመራሮች ከቤቱ ሲወጡ ታይተው ፎቶውም በማህበራዊ ድህረ-ገፅ ተለቋል።
[Goal]




ካርሎ አንቾሎቲ ኤቨርተንን ለማሰልጠን ተስማሙ

ስካይ ስፖርትስ እንደዘገበው የቀድሞው የቼልሲ ፥ የኤሲ ሚላን ፥ የሪያል ማድሪድ  እና ናፖሊ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ኤቨርተንን ለማሰልጠን በመርህ ደረጃ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
[Sky Sports]




ቻይናውያን ኦዚል ላይ የስድብ ናዳ እያወረዱበት ነው


የአርሰናሉ አማካይ በኢንስታ ግራም ገፁ ላይ ቻይና በሀገሪቷ ከሚገኙ ህዝቦች ኡግሁር የተባለው እና ሙስሊሞች የሚበዙበትን ቦታ ለይታ ሙስሊሞች እያሰቃየች መሆኑን መግለፁን ተከትሎ በቻይና መንግስት እና በቻይና  በሚገኙ የአርሰናል ደጋፊዎች እየተተቸ ነው።የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትርም "ኦዚል የተሳሳተ መረጃ ደርሶታል" ሲሉ ተናግረዋል።
[Goal]





ማራዶና የሀገሩ ልጅ የሆነው ፖቼቲንሆ "የዓለማችን ትልቁን ክለብ ቦካ ጁኒየርስ " ማሰልጠን አለበት አለ

ዲዬጎ ማራዶና የቀድሞው የቶተንሃም አሰልጣኝ ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ  የዓለማችንን ትልቁ ክለብ የአርጀንቲናውን ቦካ ጁኑየርስ ማሰልጠን አለበት ሲል ተናግሯል።

ፖቼቲንሆ ከቶተንሃም ጋር ከተለያየ አንስቶ ስሙ ከማን ዩናይትድ ፥ አርሰናል እና ባየርን ሙኒክ ጋር ሲያያዝ ቆይቷል።
[Goal]




ናፖሊ ቶሬራን በውሰት መውሰድ ይፈልጋል

የጣሊያኑ ክለብ ናፖሊ በአርሰናል ያልተረጋጋውን ኡራጋዊያዊ አማካይ ሉካስ ቶሬራ ለአንድ አመት በውሰት ለመውሰድ ጥያቄውን አቅርቧል።የኔፕልሱ ክለብ €3ሚ. ለመክፈልም አቅዷል።
[Football London]





"ማን ዩናይትድ ፖግባን ሸጦ ማንዙኪችን መግዛት አለበት" ፖል ፓርከር



የቀድሞው የማን ዩናይትድ ታላቅ ተጨዋች ፖል ፓርከር ማን ዩናይትድ የዓለም ዋንጫን ከሀገሩ ጋር ያሳካውን ፈረንሳዊ አማካይ ፖል ፖግባ በተገቢው ዋጋ በመሸጥ ልምድ ያለው አጥቂ ማስፈረም እንዳለበት ተናግሯል።


ፓርከር ከዴይሊ ስታር ጋር በነበረው ቆይታ

"ያወጡትን ገንዘብ ማግኘት ከቻሉ ወይም ትንሽ ከፍ ያለ እውነቱን ለመናገር ቢሸጡት የተሻለ ነው።በኔ ግምት [ፖግባ] ለማን ዩናይትድ ለመጫወት ሞራሉ እንዳለው አላሳየንም፡፡


"ስለዚህ እርሱን በመሸጥ ግብ አስቆጣሪ ወይም የጎል ዕድል የሚፈጥር ተጨዋች ማስፈረም አለባቸው።ማን ዩናይትድ በድጋሚ ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ መመለስ ከፈለገ ወደ ገበያው መውጣት አለበት" ብሏል፡፡
[Manchester Evening News]


ሳኔ ወደ ሜዳ ተመልሷል

ጀርመናዊው የማንችስተር ሲቲ አጥቂ ለሮይ ሳኔ ወደ ልምምድ ሜዳ መመለሱን እና እያገገመ መሆኑን ተናግሯል።የ23 አመቱ ተጨዋች ኮሚዩኒቲ ሺልድ ላይ የጉልበት ጉዳት አጋጥሞት ለረዥም ጊዜ ከሜዳ  መራቁ ይታወሳል።
(Manchester Evening News)



ዝላታን ናፖሊን አይቀላቀልም

የናፖሊው ፕሬዝደንት ኦላውሮ ደ ላውረንቲስ ስዊድናዊውን አጥቂ ዝላታን ኢብራሂሞቪች በነፃ ከማስፈረም ይልቅ ሌሎች ተጨዋቾችን የመግዛት ዕቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል።
(Mirror)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...