Monday, December 16, 2019

"ማን ዩናይትድ ፖግባን ሸጦ ማንዙኪችን መግዛት አለበት" ፖል ፓርከር

"ማን ዩናይትድ ፖግባን ሸጦ ማንዙኪችን መግዛት አለበት" ፖል ፓርከር



የቀድሞው የማን ዩናይትድ ታላቅ ተጨዋች ፖል ፓርከር ማን ዩናይትድ የዓለም ዋንጫን ከሀገሩ ጋር ያሳካውን ፈረንሳዊ አማካይ ፖል ፖግባ በተገቢው ዋጋ በመሸጥ ልምድ ያለው አጥቂ ማስፈረም እንዳለበት ተናግሯል።


ፓርከር ከዴይሊ ስታር ጋር በነበረው ቆይታ

"ያወጡትን ገንዘብ ማግኘት ከቻሉ ወይም ትንሽ ከፍ ያለ እውነቱን ለመናገር ቢሸጡት የተሻለ ነው።በኔ ግምት [ፖግባ] ለማን ዩናይትድ ለመጫወት ሞራሉ እንዳለው አላሳየንም፡፡


"ስለዚህ እርሱን በመሸጥ ግብ አስቆጣሪ ወይም የጎል ዕድል የሚፈጥር ተጨዋች ማስፈረም አለባቸው።ማን ዩናይትድ በድጋሚ ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ መመለስ ከፈለገ ወደ ገበያው መውጣት አለበት" ብሏል፡፡

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...