Sunday, December 15, 2019

የሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

የሀገር ውስጥ ዜናዎች


በሳምንቱ መጨረሻ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት የተደረጉ ጨዋታዎች ውጤት

ቅዳሜ

ወላይታ ድቻ 0-0 ቅዱስ ጊዮርጊስ
ድሬደዋ ከተማ 1-0 ሀዲያ ሆሳዕና
ወልቂጤ ከተማ 1-0 ፋሲል ከነማ
ሰበታ ከተማ 0-0 አዳማ ከተማ
ሀዋሳ ከተማ 1-0 ባህር ዳር ከተማ
ስሑል ሽረ 0-3 ወልዋሎ ዓዲግራት


እሁድ

ጅማ አባ ጅፋር 1-2 ሲዳማ ቡና
መቐለ 70 አ. 1-1 ኢትዮጵያ ቡና

(Soccer Ethiopia)



የውጭ ሀገር ዜናዎች



የባየርን ሙኒክ ተጨዋቾች ብራዚላዊው የ27 አመት አማካይ ፌሊፔ ኩቲንሆ በባቫሪያው ክለብ በቋሚነት እንዲፈርም ይፈልጋሉ።ኩቲንሆ ከባርሴሎና ባየርን ሙኒክን የተቀላቀለው በውሰት ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያሳየ ባለው አቋም ሙኒክ በቋሚነት ለማስፈረም አቅዷል።ኩቲንሆ ቅዳሜ ዕለት ከወርደር ብሬመን ጋር በነበረው ጨዋታ ሀትሪክ መስራቱ ይታወሳል።
(Mirror)



ትናንት በማንችስተር ሲቲ በሜዳው በሰፊ የግብ ልዩነት የተሸነፈው አርሰናል በፍሬዲ ሊዩምበርግ የመቀጠል ዕቅድ ያለው አይመስልም።አሁን እየወጡ ባሉ መረጃዎች አርሰናል የዎልቭሱን አሰልጣኝ ኑኖ ሳንቶ ኤስፕሪቶ ለመሾም እየተንቀሳቀሰ ነው።
(Express and Star)




በከፍተኛ ጫና ውስጥ የሚገኙት የዌስት ሀሙ አሰልጣኝ ማኑዌል ፔሌግሬኒ  በቦክሲንግ ደይ ክለባቸው ከክሪስታል ፓላስ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ የሚኖረው ውጤት ቀጣይ ጉዟቸውን ይወስናል።
(Guardian)







በኤቨርተን ድንቅ ጊዜን በአሰልጣኝነት እያሳለፈ ያለው ደንከን ፈርጉሰን ትናንት ከማን ዩናይትድ ጋር በነበረው ጨዋታ ሞይስ ኪንን በ19ነኛው ደቂቃ ቀይሮ ማስወጣቱ ብዙ ያነጋገረ ሲሆን ፥ አሰልጣኙ ከጨዋታው በኋላ መነጋገራቸውን ተናግሯል።
(Telegraph)




ቼልሲ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ናይጄሪያዊውን የቦርዶ የ20 አመት አጥቂ ጆሽ ማጃ ማዘዋወር ይፈልጋል።ተጨዋቹ ከዚህ በፊት በሰንደርላንድ ተጫውቷል።
(90min.com)





ሊቨርፑል በብዙ ክለቦች አይን ውስጥ የገባውን የኮንቬንትሪውን እንግሊዛዊ የ19 አመት ተከላካይ ሳም ማክ ካሉም የማዘዋወር ፍላጎት አለው።ክሎፕ የተከላካይ መስመራቸው ላይ ወጣት ተጨዋቾችን ማካተት ይፈልጋሉ።
(90min.com)





የፈረንሳዩ አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሾ ለ33 አመቱ አጥቂ ኦሊቪየር ዢሩ ከቼልሲ በጥር ወር የዝውውር መስኮት እንዲወጣ ነግሮታል።በቂ የመሰለፍ ዕድል በፍራንክ ላምፓርድ የተነፈገው ዢሩ ስሙ ከአንቶኒዮ ኮንቴው ኢንተር ሚላን ጋር በስፋት ተያይዟል።
(Mirror)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...