ሊቨርፑል ትናንት በቦክሲንግ ዴይ ጨዋታ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ተከታዩን ሌስተር ሲቲን 4ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሽንፏል።ቀያዮቹ ጨዋታው እንደሚከብዳቸው ቢገመትም በቀላሉ ጨዋታውን በድል ተወጥተዋል።ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ አንድ ግብ በማስቆጠር እና ሁለት አሲስት በማድረግ ድንቅ ምሽት ያሳለፈ ሲሆን ሮበርቶ ፈርሚንሆ ደሞ ክሎፕ ክለቡን ከያዙ 500ኛውን ግብ አስቆጥሯል።ከዚህ በኋላ ሊቨርፑልን ማን ሊያቆመው ይችላል?
ትናንት ማንቸስተር ዩናይትድም ወደ ድል ተመልሷል።በኦልድ ትራፎርድ ኒውካስትልን 4ለ1 የረቱ ሲሆን ፖል ፖግባ ከሶስት ወራት ጉዳት በኋላ ወደ ሜዳ ተመልሶ መጫወት ችሏል።
የአርሰናሉ አማካይ ግራኒት ዣካ ወኪል ስዊዘርላንዳዊው አማካይ ወደ ሀርታ በርሊን ለመዘዋወር መስማማቱን ይፋ አድርጓል።ዣካ በተለይ ከአርሰናል ደጋፊዎች ጋር እሰጣ እገባ ውስጥ መግባቱ ይታወሳል።
(Blick, via Mirror)
ቼልሲ ከፓሪሰን ዤርመን ጀርመናዊውን አማካይ ድራክስለር እና ሴኔጋላዊውን አማካይ ኢድሪሳ ጋና ጉዌ ከማዘዋወር ይፈልጋል።
(Star)
የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የጁቬንትሱን ፈረንሳዊ አማካይ አድናን ራቢዪ በጥር ወር የዝውውር መስኮት በውሰት ማምጣት ይፈልጋል።
(Times - subscription required)
የቼልሲው አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ብራዚላዊውን የክንፍ አጥቂ ዊልያን በስታንፎርድ ብሪጅ ለማቆየት በአዲስ ኮንትራት ጉዳይ ድርድር ላይ መሆናቸውን ተናግሯል።ዊልያን በቼልሲ ያለው ኮንትራት በአመቱ መጨረሻ ያበቃል።
(Mail)
የማንችስተር ሲቲው ጀርመናዊ የክንፍ አጥቂ ለሮይ ሳኔ እስከ አመቱ መጨረሻ በክለቡ እንደሚቆይ እና በአመቱ መጨረሻ ክረምት ላይ ግን ወደ ባየርን ሙኒክ በ£85ሚ. እንደሚዘዋወር ይጠበቃል።
(Star)
የጉልበት ጉዳት ያጋጠመው ቤልጄሚያዊው አጥቂ ኤድን ሀዛርድ እስከ የካቲት አጋማሽ ከሜዳ ውጪ ይሆናል ተብሏል።ሀዛርድ በሪያል ማድሪድ ቤት አስቸጋሪ ጊዜን በማሳለፍ ላይ ይገኛል።
(Marca)
በውሰት ለሁለት አመት ለሪያል ቤቲስ የተሰጠው ማርቲን ኦዴጋርድ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ወደ ሪያል ማድሪድ እንደሚመለስ ይጠበቃል።ኦዴጋርድ በቤቲስ ቤት ድንቅ ጊዜን በማሳለፍ ላይ ይገኛል።
(AS)
No comments:
Post a Comment