Saturday, December 28, 2019
የዕለተ ቅዳሜ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች
ትናንት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቸስተር ሲቲ በዎልቭስ መሸነፉን ተከትሎ የውሃ ሰማያዊዎቹ የነጥብ ልዩነት ከሊቨርፑል ጋር 14 ነጥብ ሆኗል።ሊቨርፑል አንድ ቀሪ ጨዋታ ያለው ሲሆን ያንን ካሸነፈ ልዩነቱ 17 ነጥብ ይሆናል።
ስሙ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ተደጋግሞ ሲያያዝ የነበረው ኖርዌያዊው የ19 አመት የሬድ ቡል ሳልዝቡርግ አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ ወደ ጁቬንትስ ለመዘዋወር ከጫፍ መድረሱን የጣሊያን ሚዲያዎች በሰፊው በመዘገብ ላይ ናቸው።
(Tuttosport, via Express)
አርሰናል ፣ ኒውካስትል ዩናይትድ እና ፓሪሰን ዤርመን ብራዚላዊውን የ23 አመት አጥቂ ኤቨርተን ሶረስ ለማዘዋወር በተደጋጋሚ ቢሞክሩም ክለቡ ግሬሚዮ ግን ለመሸጥ ፍላጎት አላሳየም።
(Newcastle Chronicle)
ዎልቭስ ደቡብ ኮሪያዊውን የሬድ ቡል ሳልዝበርግ አጥቂ ሁዋንግ ሂ ቻን ለማዘዋወር ከስምምነት ላይ ደርሷል።ዎልቭስ የ23 አመቱን ተጨዋች በውል ማፍረሻው £23ሚ. ነው ለማዘዋወር የተስማማው።
(Hamburger Morgenpost, via Birmingham Mail)
ቺሊያዊው የዌስት ሀም አሰልጣኝ ማኑዌል ፔሌግሬኒ በቅርቡ እንደሚሰናበቱ የሚጠበቅ ሲሆን ዴቪድ ሞይስ እንደሚተኳቸው ይጠበቃል።
(Telegraph)
አዲሱ የኤቨርተን አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በናፖሊ ሳሉ ቁልፍ ተጨዋቻቸው የነበረውን ጣሊያናዊውን የጨዋታ ቀማሪ ሎሬንዞ ኢንሴኚ ወደ ክለባቸው ለማምጣት ይፈልጋሉ።
(Le10 Sport, via Star)
በቼልሲ በዘንድሮው አመት በቋሚነት የመሰለፍ ዕድል ያጣው የ32 አመቱ ስፔናዊ ፔድሮ ወደ ቀድሞው ክለቡ ባርሴሎና መመለስ ይፈልጋል።
(L'Esportiu, via Mail)
ማንቸስተር ዩናይትድ እና ፓሪሰን ዤርመን የሌስተር ሲቲውን የቀኝ መስመር ተከላካይ ሪካርዶ ፔሬራ ለማዘዋወር ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን ሌስተር ሲቲ ተጨዋቹን የሚሸጠው በአመቱ መጨረሻ መሆኑን አሳውቋቸዋል።
(Le10 Sport, via Star)
የጉልበት ጉዳት ያጋጠመው ቤልጄሚያዊው አጥቂ ኤድን ሀዛርድ እስከ የካቲት አጋማሽ ከሜዳ ውጪ ይሆናል ተብሏል።ሀዛርድ በሪያል ማድሪድ ቤት አስቸጋሪ ጊዜን በማሳለፍ ላይ ይገኛል።
(Marca)
በውሰት ለሁለት አመት ለሪያል ቤቲስ የተሰጠው ማርቲን ኦዴጋርድ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ወደ ሪያል ማድሪድ እንደሚመለስ ይጠበቃል።ኦዴጋርድ በቤቲስ ቤት ድንቅ ጊዜን በማሳለፍ ላይ ይገኛል።
(AS)
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል
"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...

No comments:
Post a Comment