ማን ዩናይትድ ዴንማርካዊውን አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን በአመቱ መጨረሻ የማዘዋወር ዕድል አለው።የ27 አመቱ አማካይ በቶተንሃም ያለው ኮንትራት በአመቱ መጨረሻ ስለሚጠናቀቅ በነጻ ቀያይ ሰይጣኖቹን መቀላቀል ይችላል።
(Sunday Telegraph)
የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን የፖል ፖግባን የዝውውር ጉዳይ እንደተወው ተገልጿል።ምክንያቱ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት ድንቅ ጊዜን በበርናቢዮ እያሳለፈ ያለውን ኡራጋዊውን አማካይ ፌዴሪኮ ቫልቬርዴ ፖግባ ከመጣ እድገቱ ያንሳል ብሎ በመስጋት ነው።
(AS)
አዲሱ የኤቨርተን አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ከማን ዩናይትድ የትኛውም ገንዘብ ቢመጣ ብራዚላዊውን አጥቂያቸውን ሪቻርልሰንን ማጣት አይፈልጉም።
(Sun on Sunday)
ትናንት ዌስት ሃም ቺሊያዊውን አሰልጣኝ ማኑዌል ፔሌግሬኒ አሰናብቷል።ቶኒ ፕሉስ ወይም ዴቪድ ሞይስ ቀጣዩ የመዶሻዎቹ አሰልጣኝ እንደሚሆኑ ይጠበቃሉ።
(Sunday Telegraph)
እንግሊዛዊው የሊቨርፑል የቀኝ መስመር ተከላካይ ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ በሊቨርፑል ቤት የእግር ኳስ ህይወቱን በመጨረስ የክለቡ ሌጀንድ መሆን እንደሚፈልግ ተናግሯል።የ21 አመቱ ተከላካይ በክሎፕ ቡድን ውስጥ ቁልፍ ከሆኑ ተጨዋቾች መሀከል ነው።
(Sportbladet, via Independent)
የጁቬንትሱ አሰልጣኝ ማውሩዚዮ ሳሪ ከቀድሞው ክለባቸው ቼልሲ ፈረንሳዊውን የ33 አመት አጥቂ ኦሊቪየር ዢሩ ወደ አሮጊቷ ማምጣት ይፈልጋሉ።
(La Stampa - in Italian)
ባየርን ሙኒክ፣ጁቬንትስ እና ፓሪሰን ዤርመን ጀርመናዊውን የ27 አመት የባርሴሎና ግብ ጠባቂ ማርክ አንድሬ ቴር ስቴገን ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።የካታላኑ ክለብ ግን ግብ ጠባቂውን የመሸጥ ፍላጎት ያለው አይመስልም።
(Mundo Deportivo - in Spanish)
ሊቨርፑል ናይጄሪያዊውን ቪክቶር ኦሲሜህን ከሊል ለማዘዋወር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።
(Sunday Express)
የጣሊያኑ ፊዮረንቲና አርጀንቲናዊውን የማንቸስተር ዩናይትድ ተከላካይ ማርኮስ ሮሆ ለማዘዋወር ፍላጎት አለው።ይህ ዝውውር ሊፈጸም የሚችለው ግን ክረምት ላይ ነው።
(La Nazione, via Football Italia)
No comments:
Post a Comment