Sunday, December 29, 2019

የዕለተ ሰኞ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች



ባርሴሎና የርገን ክሎፕን ክረምት ላይ በአሰልጣኝነት የመቅጠር ፍላጎት እንዳለው ካታላን ዘመሙ ጋዜጣ ሙንዶ ዲፖርቲቮ ዘግቧል።ዘንድሮው በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ድንቅ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያለውን ሊቨርፑል የሚመሩት ክሎፕ ግን በቀያዮቹ ቤት በቅርቡ አዲስ ኮንትራት መፈረማቸው ይታወሳል።
(Mundo Deportivo)





ፔፕ ጋርዲዮላን የማሰናበት ዕቅድ እንደሌላቸው የማንቸስተር ሲቲው ቺፍ ፌሪያን ሶሪያኖ ተናግረዋል።በዘንድሮው አመት ከባድ ጊዜን በኤቲሀድ እያሳለፈ ያለው ጋርዲዮላ በተለይ ከተጨዋቾች ጋር እሰጣ እገባ ውስጥ መግባት የጀመረ ሲሆን በውሃ ሰማያዊዎቹ ቤት የመጨረሻው አመት ሊሆን እንደሚችል በስፋት እየተነገረ ነው።
(Goal)





ብራዚላዊው ተከላካይ ማርኪኒሆስ በፓሪሰን ዤርመን ለተጨማሪ አመታት እንዲቆይ አዲስ ኮንትራት ቀርቦለታል።የ25 አመቱ ተከላካይ ከዚህ በፊት የቀረበለትን ውል ውድቅ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ግን ከፍተኛ ደሞዝ ነው ክለቡ ያሰናዳለት።
(Le10Sport)





ኮሎምቢያዊው ሀሜስ ሮድሪጌዝ በሪያል ማድሪድ የሚኖረው ቆይታ በቀጣዮቹ አራት ጨዋታዎች ይወሰናል።ከ2014ቱ የዓለም ዋንጫ በኋላ ሪያል ማድሪድን ተቀላቅሎ የነበረው ሀሜስ በውሰት ለተለያዩ ክለቦች የተሰጠ ሲሆን በበርናቢዮ ስኬታማ ጊዜን እያሳለፈ አይደለም።
(Don Balon)






ኤርሊንግ ሀላንድ ወደ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ለመዘዋወር ከስምምነት ላይ ደረሰ።በዘንድሮ አመት ድንቅ ጊዜን በሬድ ቡል ሳልዝበርግ አሳልፎ የነበረው ሀላንድ በተለይ ስሙ ከማን ዩናይትድ ጋር ሲያያዝ የቆየ ቢሆንም በመጨረሻ ግን ማረፊያው የጀርመኑ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ መሆኑ ተረጋግጧል።
(the Sun)





ፔሌግሬኒን ያሰናበተው ዌስት ሀም ዴቪድ ሞይስን በዋና አሰልጣኝነት ለመቅጠር ከጫፍ ደርሷል።መዶሻዎቹ ለቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ እና የኤቨርተን አሰልጣኝ የ18 ወራት ኮንትራትም አቅርበውለታል።
(Football Insider)






ሚኬል አርቴታ ግራኒት ዣካ በክለቡ እንዲቆይ ይፈልጋል።ትናንት አርሰናል በሜዳው ኤምሬትስ በለንደን ደርቢ በቼልሲ ሲሸነፍ ዣካ አለመኖሩን ተከትል የተጨዋቹ ስም በስፋት ከዝውውር ጋር በመያያዝ ላይ ነበር።ሆኖም አርቴታ ከጨዋታው በኋላ የ27 አመቱ አማካይ በክለቡ ይቆያል ብሏል።
(Goal)






ቼልሲ ታሚ ኤብራሃምን አዲስ ኮንትራት ያቀረበለት ቢሆንም በክፍያ ጉዳይ ግብ እስካሁን መስማማት አልቻሉም። እንግሊዛዊው አጥቂ በሳምንት £120,000 እንዲከፈለው ነው የሚፈልገው።
(The Athletic)





አትሌቲኮ ማድሪድ ሴድሪክ ባካምቡን በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር ከጫፍ ደርሷል።ባካምቡ በዘንድሮው አመት በቻይና 16 ግቦችን በ26 ጨዋታዎች አስቆጥሯል።
(Deportes Cuatro)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...