Monday, December 30, 2019

የዕለተ ሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሀና ልጅ)


ባርሴሎና ብራዚላዊውን የ27 አመት አጥቂ ኔይማር በድጋሚ ወደ ካምፕ ኑ የሚያዘዋውረው አርጀንቲናዊው ጥበበኛ ሊዮኔል ሜሲ ከባርሴሎና የሚለቅበትን ጊዜ ካሳወቀ በኋላ ነው።በዓለም የተጨዋቾች ሪከርድ ዋጋ ፓሪሰን ዤርመንን የተቀላቀለው ኔይማር  ስኬታማ ጊዜን በፈረንሳዩ ክለብ እያሳለፈ አይደለም።
(Sport)




ሁለቱ የሰሜን ለንደን ክለቦች አርሰናል እና ቶተንሃም ፈረንሳዊውን የራ.ቢ ሌብዚክ የመሀል ተከላካይ ዳዮት ፓሜካኖ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።የ21 አመቱን ተከላካይ ማንቸስተር ሲቲም የሚፈልገው ሲሆን £55ሚ. ደግሞ በሌብዚክ የተጠየቀው የዝውውር ሂሳብ ነው።
(Daily Star)





ኒውካስትል ዩናይትድ ለ27 አመቱ አማካይ ጆንጂዮ ሼልቪ አዲስ ኮንትራት አቅርቦለታል።ሼልቪ በሴንት ጄምስ ፓርክ እስከ 2021 የሚያቆይ ኮንትራት ከወዲሁ ያለው ሲሆን ኒውካስትል ግን አዲስ ኮንትራት አቅርቦለታል።
(Chronicle)





ትናንት በይፋ ቦሩሲያ ዶርትሙንድን የተቀላቀለው ኤርሊንግ ሀላንድ በማን ዩናይትድ ከፍተኛ ደሞዝ ቀርቦለት ዝውውሩን ውድቅ አድርጎ ወደ ዶርትሙንድ እንደተቀላቀለ ተገልጿል።ሀላንድ ይህንን ያደረገው ለዕድገቱ የጀርመኑ ክለብ እንደሚሻል በማሰብ ነው።
(Independent)






አርሰናል የአትሌቲኮ ማድሪዱን አጥቂ ቶማስ ሌማር በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ፍላጎት ያለው ሲሆን አትሌቲኮ ለተጨዋቹ የጠየቀው ገንዘብ ግን ከፍተኛ ነው ተብሏል።ቶማስ ሌማር ከሞናኮ አትሌቲኮ ማድሪድን ከተቀላቀለ ጀምሮ ደካማ ጊዜን ነው እያሳለፈ የሚገኘው።
(AS, via Mirror)




ፍራንክ ላምፓርድ ከ19 አመቱ የቀኝ መስመር ተከላካይ ታሪቅ ላምቴይ ጋር በአዲስ ኮንትራት ጉዳይ ክለቡ ንግግር ላይ መሆኑን ተናግሯል።ላምቴይ በቼልሲ እስከ አመቱ መጨረሻ ብቻ የሚያቆይ ኮንትራት ነው ያለው።
(Goal)





ምንም እንኳን ስሙ በስፋት ከጀርመኑ ክለብ ሀርታ በርሊን ጋር ቢያያዝም አርቴታ ግራኒት ዣካ በአርሰናል እንደሚቆይ ተናግሯል።ስዊዘርላንዳዊው አማካይ በአርሰናል የሚኖረው ቆይታ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ከገባ ሰነባብቷል።
(Football London)






ባርሴሎና የርገን ክሎፕን ክረምት ላይ በአሰልጣኝነት የመቅጠር ፍላጎት እንዳለው ካታላን ዘመሙ ጋዜጣ ሙንዶ ዲፖርቲቮ ዘግቧል።ዘንድሮው በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ድንቅ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያለውን ሊቨርፑል የሚመሩት ክሎፕ ግን በቀያዮቹ ቤት በቅርቡ አዲስ ኮንትራት መፈረማቸው ይታወሳል።
(Mundo Deportivo)





ፔፕ ጋርዲዮላን የማሰናበት ዕቅድ እንደሌላቸው የማንቸስተር ሲቲው ቺፍ ፌሪያን ሶሪያኖ ተናግረዋል።በዘንድሮው አመት ከባድ ጊዜን በኤቲሀድ እያሳለፈ ያለው ጋርዲዮላ በተለይ ከተጨዋቾች ጋር እሰጣ እገባ ውስጥ መግባት የጀመረ ሲሆን በውሃ ሰማያዊዎቹ ቤት የመጨረሻው አመት ሊሆን እንደሚችል በስፋት እየተነገረ ነው።
(Goal)





ብራዚላዊው ተከላካይ ማርኪኒሆስ በፓሪሰን ዤርመን ለተጨማሪ አመታት እንዲቆይ አዲስ ኮንትራት ቀርቦለታል።የ25 አመቱ ተከላካይ ከዚህ በፊት የቀረበለትን ውል ውድቅ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ግን ከፍተኛ ደሞዝ ነው ክለቡ ያሰናዳለት።
(Le10Sport)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...