ማን ዩናይትዶች ኤርሊንግ ሀላንድን ካዘዋወሩ ፖል ፖግባን እንዳያጡ ሰግተዋል፡፡የሁለቱም ተጨዋቾች ወኪል ሚኖ ራዮላ ሲሆን ፈረንሳዊው አማካይ ስሙ በስፋት ከሪያል ማድሪድ እና ጁቬንትስ ጋር ለወራት ሲያያዝ ቆይቷል፡፡
(Daily Star)
በዘንድሮው አመት ከወትሮው የተዳከመ የሚመስለው የፔፕ ጋርዲዮላው ማንቸስተር ሲቲ የተከላካይ መስመሩን ለማጠናከር የተለያዩ ተጨዋቾችን ለማዘዋወር እየሰራ ይገኛል፡፡የቪያሪያሉ ፓዎ ቶረስ እና የቤኔፊካው ሩበን ዲያዝ ደግሞ ከውሃ ሰማያዊዎቹ ጋር ስማቸው በተደጋጋሚ እየተነሳ ነው፡፡
(Telegraph)
በስቴቨን ዤራርድ የሚመራው የስኮትላንዱ ክለብ ሬንጀርስ ፈረንሳዊውን አጥቂ ኦሊቪየር ዢሩ ከቼልሲ ለማዘዋወር ድርድር ጀምሯል ፡፡ዢሩ በፈረንጆቹ አዲስ አመት በስታንፎርድ ብሪጄ ያለው ውል ያበቃል፡፡
(Daily Record)
ጆዜ ሞሪንሆ በዝውውር መስኮቱ ክለባቸው ቶተንሀም እምብዛም እንደማይሳተፍ ፍንጭ ሰጥተዋል ፡፡ፖርቱጋላዊው አሰልጣኝ "በዝውውሩ ንጉስ አንሆንም" ሲሉም ተናግረዋል ፡፡
(Goal)
ቼልሲ ጄደን ሳንቾን ለማዘዋወር ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ የተጠየቀውን £100ሚ. ለመክፈል ዝግጁ አይደለም ፡፡ሰማያዊዎቹ ተጨዋቹን አጥብቀው ቢፈልጉትም የተጠየቁት ገንዘብ ግን እንደተጋነነ ያስባሉ፡፡ቼልሲ ዊልፍሬድ ዛሃን እና ቲም ዋርነርንም እንደ አማራጭነት ይዟል፡፡
(Express Sport)
አርሰናል ሜሱት ኦዚልን እና ሽኮድራን ሙስጣፊን በጥር ወር የዝውውር መስኮት ሊለቅ ይችላል፡፡አዲሱ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድኑን እንደ አዲስ ለማዋቀር እየሞከረ ሲሆን ሁለቱ ተጨዋቾች ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
(football London)
ማን ዩናይትድ ዛሬ ከኒውካስትል ጋር በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቦክሲንግ ዴይ ጨዋታ ምን አይነት አሰላለፍ ይከተላል?
ዛሬ በቦክሲንግ ዴይ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠኝ ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን በኦልድ ትራፎርድ ማን ዩናይትድን ኒውካስትል ዩናይትድን ያስተናግዳል፡፡
ባለፈው ጨዋታ በዋትፎርድ የተረቱት የኦሌ ጉናር ሶልሻየር ልጆች የዛሬውን ጨዋታ በድል የመወጣት ሀላፊነት ተሰጥቷቸው ወደ ሜዳ ይገባሉ፡፡
በዩናይትድ በኩል በበጎ መልኩ እየተነሳ የሚገኘው የፖል ፖግባ ወደ ሜዳ መመለስ ሲሆን ከሶስት ወራት ጉዳት በኃላ ዛሬ እንደሚሰለፍ ይጠበቃል፡፡
በዛሬው ጨዋታ ከዋትፎርድ ጋር ደካማ የነበረው ዴቪድ ዴሄያ በሮሜሮ ሊተካ እንደሚችልም እየተነገረ ነው፡፡
በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ሴንት ጄምስ ፓርክ ላይ ኒውካስትል ማን ዩናይትድን 1-0 አሸንፎ ነበር፡፡
(Manchester Evening News)
አርሰናል በጥር ወር የዝውውር መስኮት የጁቬንትሱን አማካይ አድናን ራቢዮ በውሰት ለማስፈረም እየሞከረ ነው፡፡ፈረንሳዊው አማካይ ከፓሪሰን ዤርመን ጁቬንትስን ከተቀላቀለ አንስቶ በቂ የመሰለፍ ዕድል አልተሰጠውም ፡፡
(The Times)
No comments:
Post a Comment