ባለፈው አስር አመት የታዩ 10 የፕሪሚየር ሊግ ምርጥ አሰልጣኞች
ታዋቂው ጋዜጣ ፎር ፎር ቱ ባለፈው አስር አመት የታዩ 10 ምርጥ አሰልጣኞችን በብዙ መመዘኛዎች ካየ በኋላ ይፋ አድርጓል።
እንደ ጋዜጣው ዘገባ ከሆነ 97 አሰልጣኞች ባለፈው አስር አመት የነበሩ ሲሆን ስምንት አሰልጣኞች ደግሞ የሊጉን ዋንጫ አሳክተዋል።
ጋዜጣው አርሰን ቬንገርን ያላካተተ ሲሆን ምክንያቱን ሲያስረዳ ምንም እንኳን ቬንገር ከምንጊዜም ምርጦች ቢሆኑም ይሄ ዳታ ከ2010 በኋላ ያሉ አሰልጣኞች ብቻ የተካተቱበት ስለሆነ ፈረንሳዊው አሰልጣኝ ደግሞ ከ2010 በኋላ እምብዛም አመርቂ ጊዜን አላሳለፉም ብሏል።
ደረጃው ይህንን ይመስላል
10.ክላውዲዮ ራኒዬሪ
9.ሮይ ሆዲሰን
8.ጆዜ ሞሪንሆ
7.ብሬንዳን ሮጀርስ
6.ራፋኤል ቤኒቴዝ
5.አንቶኒዮ ኮንቴ
4.ሰር አሌክስ ፈርጉሰን
3.ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ
2.የርገን ክሎፕ
1.ፔፕ ጋርዲዮላ
No comments:
Post a Comment