Friday, December 13, 2019

"ማንቸስተር ዩናይትድ ምናልባትም የዓለማችን የምንጊዜም ታላቁ ክለብ ነው" ፖል ፖግባ

"ማንቸስተር ዩናይትድ ምናልባትም የዓለማችን የምንጊዜም ታላቁ ክለብ ነው" ፖል ፖግባ



ፖል ፖግባ ታዳጊ ተጨዋቾች ለማን ዩናይትድ ለመሰለፍ ዕድሉን ሲያገኙ በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው ተናግሯል።ምክንያቱ ደግሞ 'ዩናይትድ ምናልባትም የምንጊዜው ታላቁ ክለብ ስለሆነ' ነው ብሏል።
ማን ዩናይትድ ነገ በአጠቃላይ በስኳዱ ውስጥ ቢያንስ አንድ ከአካዳሚ ያደገ ተጨዋች የሚኖርበት በአጠቃላይ በክለቡ ታሪክ 4,000ኛ ጨዋታውን ነው የሚያደርገው።

ባለፈው ሐሙስ በዩሮፓ ሊግ 4ለ0 ሲያሸንፍም በስኳዱ ውስጥ ዘጠኝ ታዳጊ የአካዳሚ ተጨዋቾች ነበሩ።

የ16 አመት ታዳጊ ሳለ ዩናይትድን የተቀላቀለው ፖግባም ታዳጊዎቹን ጠንክረው እንዲሰሩ ምክሩን ለግሷል።

"የመጀመሪያው ቡድን ውስጥ ያሉትን ታዳጊዎች ሁልጊዜም እንዲህ እላቸዋለሁ 'አሁን የተሰጣችሁን ዕድል ሌሎች ተጨዋቾች ሳይመጡ በአግባቡ ተጠቀሙበት።' አንድ ተጨዋች ሲጎዳ ነው ብዙ ጊዜ ታዳጊዎች የመሰለፍ ዕድል የሚያገኙት ፥ ያንን ዕድል ከተጠቀምክበት በቡድኑ ውስጥ ቋሚ ሆነህ አጠቃላይ የእግር ኳስ ህይወትህን መስመር ታስይዛለህ።"

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...