አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
የርገን ክሎፕ በሊቨርፑል ለአምስት አመት የሚያቆያቸውን አዲስ ኮንትራት ፈርመዋል።
ጀርመናዊው አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በአንፊልድ እስከ 2024 የሚያቆያቸውን ኮንትራት ተፈራርመዋል።በአሁኑ ሰዓት ሊጉን በስምንት ነጥብ ልዩነት በመምራት ላይ እና በሻምፒዮንስ ሊግ 16 ውስጥ ለገቡት ቀያዮቹ በጎ ዜና ነውም ተብሏል።ክሎፕ ከፊርማው በኋላ ሰፋ ያለ አስተያየት የሰጡ ሲሆን በክለቡ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
(Goal)
ማርቲን ኦዴጋርድ ለሪያል ማድሪድ ከመፈረሙ በፊት ባርሴሎና ሊያዘዋውረው ሞክሮ እንደነበር ተናገረ።
ኖርዌያዊው አጥቂ በአንድ ወቅት የዓለም መነጋገሪያ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን 2015 ላይ ሪያል ማድሪድን ከተቀላቀለ በኋላ ግን አንድ ጊዜ ብቻ ነው በሊጉ መሰለፍ የቻለው።አብዛኛውን ጊዜውንም በውሰት ለሌሎች ክለቦች ተሰጥቶ ነው ያሳለፈው።
(Goal)
አትሌቲኮ ማድሪድ በጥር ወር የዝውውር መስኮት የቼልሲውን የግራ መስመር ተከላካይ ማርኮስ አሎንሶ ለማዘዋወር ይፈልጋል።አሎንሶ በዘንድሮው አመት አምስት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ብቻ ነው የመጀመሪያ ተሰላፊ የነበረው።
(Cope)
ማን ሲቲ የባርሴሎናውን የግራ መስመር ተከላካይ ሁዋን ላሪየስ ለማስፈረም እየሰራ ነው።ላሪየስ ገና የ15 አመት ታዳጊ ሲሆን ወደ ፊት ትልቅ ተጨዋች እንደሚሆን ብዙ እየተባለለት ይገኛል።ተጨዋቹ በአሁኑ ሰዓት በባርሴሎና ሁለተኛው ቡድን በመጫወት ላይ ሲሆን ፔፕ ጋርዲዮላ በጥብቅ ፈልጎታል።
(SPORT)
ሪያል ማድሪድ በቀጣዩ ወር ሉካ ዮቪችን በውሰት ለሌላ ክለብ የመስጠት ዕቅድ አለው።ዮቪች ከኢንትራክት ፍራንክፈርት በ£54ሚ. ሎስ ብላንኮዎቹን ከተቀላቀለ አንስቶ እስካሁን ያስቆጠረው አንድ ግብ ሲሆን እጅግ ደካማ ጊዜን ነው እያሳለፈ የሚገኘው።
(Calcio Mercato)
ካርሎ አንቾሎቲ ዛሬ ከኤቨርተኑ ባለቤት ፋራድ ሞሺሪ እና ሊቀመንበሩ ቢል ኪንራይት ጋር ለመነጋገር ወደ ለንደን እንደመጡ ታውቋል።ከናፖሊ በዚህ ሳምንት የተሰናበቱት ካርሊቶ በመርሲሳይዱ ክለብ ከሚፈለጉ አሰልጣኞች አንዱ ናቸው።
(The Sun)
በሳምንቱ መጨረሻ በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች የሚደረጉ ጨዋታዎች መርሃ - ግብር
እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ
ቅዳሜ
ሊቨርፑል ከ ዋትፎርድ - 9:30
በርንሌይ ከ ኒውካስትል - 12:00
ቼልሲ ከ በርንማውዝ - 12:00
ሌስተር ሲቲ ከ ኖርዊች ሲቲ - 12:00
ሼፍልድ ዩናይትድ ከ አስቶን ቪላ - 12:00
ሳውዝሀምተን ከ ዌስት ሀም ዩናይትድ - 12:00
እሁድ
ማን ዩናይትድ ከ ኤቨርተን - 11:00
ዎልቭስ ከ ቶተንሃም - 11:00
አርሰናል ከ ማን ሲቲ - 1:30
ሰኞ
ክሪስታል ፓላስ ከ ብራይተን - 4:45
ከዚህ በመቀጠል ደግሞ ከሌሎች ሊጎች የተመረጡ ጨዋታዎችን መርሃ ግብር እንጠቁማችሁ
ስፔን ላሊጋ
ቅዳሜ
ሪያል ሶሴዳድ ከ ባርሴሎና - 12:00
አትሌቲክ ቢልባኦ ከ አይባር - 2:30
አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ኦሳሱና - 5:00
እሁድ
ሲቪያ ከ ቪያሪያል - 2:30
ቫሌንሲያ ከ ሪያል ማድሪድ - 5:00
ጣሊያን ሴሪ ኤ
ቅዳሜ
ናፖሊ ከ ፓርማ - 12:00
እሁድ
ኤሲ ሚላን ከ ሳሱሎ - 11:00
ቦሎኛ ከ አታላንታ - 11:00
ጁቬንትስ ከ ዩዲኒዜ - 11:00
ሮማ ከ ስፓል - 2:00
ፊዮረንቲና ከ ኢንተር ሚላን - 4:45
ቡንደስሊጋ
ቅዳሜ
ኮሎኝ ከ ባየርን ሊቨርኩሰን - 11:30
ሜንዝ ከ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ - 11:30
ባየርን ሙኒክ ከ ወርደር ብሬመን - 11:30
ማን ዩናይትድ የቦሩሲያ ዶርትሙንዱን የ19 አመት እንግሊዛዊ የክንፍ አጥቂ ጄደን ሳንቾ በቀጣዩ ወር በሚከፈተው የጥር ወር የዝውውር መስኮት ወደ ኦልድ ትራፎርድ እንደሚያመጣ ተማምኗል።ቀያይ ሰይጣኖቹ በተጨማሪም ዴንማርካዊውን የቶተንሃም አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰንንም የማዘዋወር ዕቅዱ አላቸው።
(Mirror)
ፔፕ ጋርዲዮላ ኮንትራቱን በማቋረጥ በአመቱ መጨረሻ ማንቸስተር ሲቲን ሊለቅ ይችላል፡፡ውሃ ሰማያዊዎቹን ከተቀላቀለ አንስቶ ሁለት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ያሳካው ፔፕ በዘንድሮው አመት ግን ደካማ ጊዜ ነው በኢቲሀድ እያሳለፈ ያለው።
(Mail)
በፓሪሰን ዤርመን እምብዛም ስኬታማ ያልሆነው የ27 አመቱ ብራዚላዊ ኢንተርናሽናል ኔይማር በፓሪሱ ክለብ ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል።የዓለማችን የዝውውር ሪከርድ በሆነ ዋጋ ፔዤ የተቀላቀለው ኔይማር ስሙ በስፋት ከቀድሞው ክለቡ ባርሴሎና እና ከሌሎች ሐያላን የአውሮፓ ክለቦች ጋር ይያያዛል።
(AS)
በአሁኑ ሰዓት በቻይናው ክለብ ሻንጋይ ሊውንግስ የሚገኘው ቤልጄሚያዊውን አማካይ ማርዋን ፌይላኒን ለማዘዋወር ቶተንሃም ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ጆዜ ሞሪንሆ በማን ዩናይትድ ሳሉ ከተጨዋቹ ጋር አንድ ላይ መስራታቸው ይታወሳል።
(Eleven Sports via Evening Standard)
በቼልሲ ያለው ኮንትራት በዓመቱ መጨረሻ የሚያበቃው ስፔናዊው የ32 አመት አጥቂ ፔድሮ ሮድሪጌዝ በድጋሚ በባርሴሎና የመጫወት ዕድሉን ሊያገኝ ይችላል።
(Sport)
No comments:
Post a Comment