Monday, December 30, 2019

የዕለተ ማክሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                      አቅራቢ-አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


እንግሊዛዊው አጥቂ ታሚ ኤብራሃም በቼልሲ እስካሁን አዲስ ኮንትራት ያልፈረመው በቅርቡ አዲስ ኮንትራት ከፈረመው የ19 አመቱ ዊንገር ካሉም ሁዲሰን ኦዶይ እኩል ሳምንታዊ £180,000 ይከፈለኝ በማለቱ ነው።
(Goal)





ማንቸስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን የ21 አመት አጥቂ ዶሚኒክ ካልቨርት ሊውን በአመቱ መጨረሻ ከኤቨርተን ለማዘዋወር ዕቅድ አለው።
(Sun)





የርገን ክሎፕ በአመቱ መጨረሻ በአንፊልድ ያለው ኮንትራት የሚያበቃው እንግሊዛዊው የ31 አመት አማካይ አዳም ላላና በሊቨርፑል እንዲቆይ አዲስ ኮንትራት እንዲቀርብለት ይፈልጋሉ።
(Telegraph)






ማንቸስተር ዩናይትድ ፖል ፖግባን በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለመሸጥ ፍላጎት እንደሌለው ያሳወቀ ሲሆን ፈረንሳዊው አማካይም የክለቡን ሀሳብ አክብሮ በኦልድ ትራፎርድ ለመሰንበት ተስማምቷል።
(Sky Sports, via Metro)





በውጥረት ውስት የሚገኙት ኤርኔስቶ ቫርቬርዴ በ2020 የሚሰናበቱ ከሆነ ባርሴሎና ሊሾማቸው ከሚችሉ አሰልጣኞች መሀከል የቀድሞው የክለቡ ሌጀንድ ቴሪ ሄንሪ ይገኝበታል።
(Sport - in Spanish)





አዲሱ የአርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በክለቡ ዋነኛ ግብ አስቆጣሪ የሆነውን ጋቦናዊውን የ30 አመት አጥቂ ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ በኤምሬትስ ለማቆየት ተግዳሮት እንደገጠመው ቴሌግራፍ ዘግቧል።
(Telegraph)






ኤቨርተን ኮሎምቢያዊውን የ28 አመት ዊንገር ሀሜስ ሮድሪጌዝ ከሪያል ማድሪድ ለማስፈረም እየሞከረ ይገኛል።አዲሱ የኤቨርተን አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ከተጨዋቹ ጋር ከዚህ ቀደም በጋራ መስራታቸው ይታወሳል።
 (El Desmarque - in Spanish)





የ29 አመቱ አርጀንቲናዊ ተከላካይ ማርከስ ሮሆ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ከማንቸስተር ዩናይትድ ይሰናበታል።በሌላ ዜና ማን ዩናይትድ ፖርቱጋላዊውን የቤኔፊካ አማካይ ጌድሰን ፈርናንዴዝ ለማዘዋወር አጥብቆ በመስራት ላይ ይገኛል።
(Manchester Evening News)





ሪያል ማድሪድ በውሰት ለዎልቨርሀምተን ሰጥቶት የነበረውን የ22 አመቱን ተከላካይ ጄሱስ ቫሌሆ ወደ በርናቢዮ ሊመልሰው ነው።ማድሪድ ይህንን የሚያደርገው ተጨዋቹ በዎልቭስ በቂ የመሰለፍ ዕድል ስላልተሰጠው ነው።
(AS - in Spanish)

1 comment:

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...