አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ቼልሲ ከቀናት በኋላ በሚከፈተው የጥር ወር የዝውውር መስኮት የአጥቂ መስመር ስፍራውን ለማጠናከር ጀርመናዊውን የራ.ቢ ሌብዚክ አጥቂ ቲሞ ዋርነር ለማዘዋወር እየሰራ ነው፡፡
(Express)
በከፍተኛ ውዝግብ ወስጥ ያለው ፈረንሳዊው የ26 አመት አማካይ ፖል ፖግባ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ማንቸስተር ዩናይትድን ለቆ የቀድሞ ክለቡን ጁቬንትስን መቀላቀል ይፈልጋል፡፡ፖግባ ከማን ዩናይትድ መልቀቁ አይቀሬ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡
(Calicomercato - in Italian)
ባርሴሎና በቀጣዩ ክረምት ኔይማርን ከፓሪሰን ዤርመን ለማዘዋወር ፍላጎት አለው፡፡ኔይማር ከፓሪሱ ክለብ መልቀቅ ይፈልጋል፡፡
(Goal)
ክሮኤሽያዊው አጥቂ ማርዮ ማንዙኪች ወደ ኳታሩ ክለብ አል ዱሀይል ተዘዋውሯል ፡፡የ33 አመቱ አጥቂ በተለይ በማንቸስተር ዩናይትድ በጥብቅ ይፈለግ ነበር፡፡
(Mail)
ማንቸስተር ዩናይትድ ለ19 አመቱ ኖርዌያዊ አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ ሳምንታዊ £200,000 አቅርቦለታል፡፡ቀያይ ሰይጣኖቹ ተጨዋቹን ከሬድ ቡል ሳልዝበርግ ለማዘዋወር ከፍተኛ ፉክክር ከሌሎች ክለቦች ገጥሟቸዋል ፡፡
(Sun)
ኢንተር ሚላን ስፔናዊውን የግራ መስመር ተከላካይ ማርኮስ አሎንሶ ከቼልሲ ለማዘዋወር እየሰራ ነው፡፡አንቶኒዮ ኮንቴ በቼልሲ ሳለ ከአሎንሶ ጋር አብረው መስራታቸው ይታወሳል፡፡
(Calciomercato)
የ32 አመቱ ኡራጋዊያዊ የፓሪሰን ዤርመን አጥቂ ኤዲንሰን ካቫኒ ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ለመዘዋወር ከጫፍ ደርሷል ፡፡
(Marca)
አርሰናል አንዳንድ ተጨዋቾችን በመሸጥ ፈረንሳዊውን የ23 አመት የሊዮን አጥቂ ሙሳ ዴምቤሌ ለማዘዋወር እየሰራ ነው፡፡አዲሱ የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የተጨዋቹ አድናቂ ነው፡፡
(Le10Sport - in French)
ኤሲ ሚላን አንጋፋውን የ38 አመት አጥቂ ዝላታን ኢብራሂሞቪች በጥር ወር የዝውውር መስኮት እንደሚያስፈርም ተማምኗል፡፡ዝላታን በኤቨርተንም በጥብቅ ይፈለጋል፡፡
(Mail)
No comments:
Post a Comment