ባርሴሎና የቀድሞውን ተጨዋቹን ኔይማር በክረምቱ የዝውውር መስኮት በድጋሚ ከፔዤ ማዘዋወር ይፈልጋል፡፡
(Mundo Deportivo - in Spanish)
የራ.ቢ ሌብዚኩ ፕሬዝዳንት ኦሊቪየር ሚንትላፍ ክለባቸው በማንችስተር ዩናይትድ በጥብቅ እየተፈለገ ያለውን የሬድ ቡል ሳልዝበርግ አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ ለማዘዋወር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።ኖርዌያዊው አጥቂ በኦሊ ጉናር ሶልሻየር በጥብቅ እንደሚፈለግ ይታወቃል ።
(Mail)
ቼልሲ ስፔናዊውን አማካይ ኢስኮ ለማዘዋወር ለሪያል ማድሪድ £44ሚ. አቅርቧል ።ሎስብላንኮዎቹ ዴንማርካዊውን አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ከስፐርስ ለማዘዋወር እየሰሩ በመሆናቸው ኢስኮን ለመሸጥ አያመነቱም።
(Mirror)
የ26 አመቱ ቦስኒያዊ የአርሰናል ተከላካይ ሳይድ ኮላሲናች በጣሊያኖቹ ክለቦች ናፖሊ እና ሮማ ይፈለጋል ።
(Sky Sports)
ሪያል ማድሪድ ለፈረንሳዊው አማካይ ፖል ፖግባ ወኪል ሚኖ ራዮላ ተጫዋቹን በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር ዝግጁ እንዳልሆነ አሳውቆታል።
(Mail)
ቶተንሀም የ22 አመቱን ፈረንሳዊ የመሀል ተከላካይ ኢሳ ዲዮፕ ለማዘዋወር £50ሚ. በዌስትሃም ተጠይቋል ።ቡድናቸው በየጨዋታው ግብ ማስተናገዱ ያሳሰባቸው ጆዜ ሞሪንሆ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አጥብቀው ይፈልጋሉ ።
(Express)
የ32 አመቱ ኡራጋዊያዊ አጥቂ ኤዲንሰን ካቫኒ ወደ ስፔኑ ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ ተዘዋውሯል ።ካቫኒ በዋንዳ ሜትራፖሊታኖ ለሶስት አመታት የሚቆይ ሲሆን የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት ለፍራሽ አዳሾቹ መሰለፍ ይጀምራል ።
(Star)
የማንቸስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ኦሊ ጉናር ሶልሻየር ክሮኤሽያዊው የጁቬንትስ አጥቂ ማርዮ ማንዙኪች ለአጭር ጊዜ ወደ ኦልድ ትራፎርድ እንዲመጣለት ይፈልጋል ።
(Express)

No comments:
Post a Comment