ጆዜ ሞሪንሆ ትናንት በቼልሲ ከተሸነፉ በኋላ አንቶኒዮ ኮንቴ በሰራው ድንቅ የአማካይ ክፍል ነው የተሸነፍነው ብለዋል ።ጆዜ ጣሊያናዊው አሰልጣኝ ኮንቴ በቼልሲ ሳለ የሰራውን የአማካይ ክፍል አሞካሽተዋል።
(Goal)
አዲሱ የአርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ቡድኑን ለማጠናከር ድረስ መርቲንስን ከናፖሊ ወደ አርሰናል ማምጣት ይፈልጋል ።የ32 አመቱ ቤልጄሚያዊ በኔፕልሱ ክለብ ያለው ኮንትራት በዚህ አመት ይገባደዳል።
(Calciomercato)
ማንችስተር ዩናይትድ እና በርካታ የጀርመን ክለቦች የበርኒንግ ሀም ሲቲውን እንግሊዛዊ የ16 አመት አማካይ ጁድ ቤሊንግሀም ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል ።
(Telegraph)
ኤቨርተን አዲሱ አሰልጣኙን ካርሎ አንቾሎቲ በዋና አሰልጣኝነት ሲሾም ጣሊያናዊው አሰልጣኝ በጥር ወር የዝውውር መስኮት የሚፈልጓቸውን ተጨዋቾች እንደሚያዘዋውርላቸዉ ቃል ገብቶላቸዋል ።
(Star)
ማን ዩናይትድ ውሉ ክረምት ላይ ለሚጠናቀቀው ሰርቢያዊ አማካይ ኒማኒያ ማቲች አዲስ ኮንትራት ማቅረብ አይፈልግም ።
(Express)
አርሰናል በጥር ወር የዝውውር መስኮት ጀርመናዊውን የባየርን ሊቨርኩሰን አጥቂ ኬቨን ቮላንድ ማዘዋወር ይፈልጋል ።
(sky sports)
ቦሩሲያ ዶርትሙንድ አጥቂውን ጄደን ሳንቾ በጥር ወር የዝውውር መስኮት መሸጥ አይፈልግም ።በዘንድሮው አመት ዘጠኝ ግብ እና ዘጠኝ አሲስት ያደረገው ሳንቾ በተለይ ከቼልሲ ጋር ስሙ በስፋት ተያይዟል ።
(Bild)
ማንችስተር ዩናይትድ እና ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ኖርዌያዊውን አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ ለማዘዋወር ከፍተኛው ዕድል ያላቸው ክለቦች ናቸው።ሀላንድ በዘንድሮው አመት በሁሉም የውድድር አይነቶች በ22 ጨዋታዎች 28 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል ።
(Bild)
No comments:
Post a Comment