Sunday, December 22, 2019

የዕለተ እሁድ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

ቼልሲ ፣ ማን ዩናይትድ እና ሊቨርፑል የ19 አመቱን እንግሊዛዊ አጥቂ ጄደን ሳንቾ ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል ።የጀርመኑ ክለብ ለዝውውሩ  €120ሚ. ጠይቋል ።
(Sun on Sunday)





ዛሬ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማን ዩናይትድ ከሜዳው ዉጪ ዋትፎርድን ለሚገጥምበት ጨዋታ ከተጓዙ ተጨዋቾች መሀከል ፖል ፖግባ አንዱ ነው።

ፖግባ ለመጨረሻ ጊዜ የቀያይ ሰይጣኖቹን ማሊያ የለበሰው ማን ዩናይትድ ከ አርሰናል ጋር 1ለ1 በተለያየበት ጨዋታ ነበር ።

ሶልሻየር ስለ ፈረንሳዊዉ አማካይ ቆይታ ተጠይቆ

"ፖግባ ምርጥ ተጨዋች ነው።የኛ ተጨዋች በመሆኑም ደስተኛ ነን።አሁን ከጉዳቱ አገግሟል ፤ ጥሩ ደረጃ ላይ ነው።በጥር ወር የዝውውር መስኮት አይሸጥም ።" ብሏል።
(Manchester Evening news)




ሚኬል አርቴታ አርሰናልን የተቀላቀለው የማንቸስተር ሲቲ አመራሮች ፔፕ ጋርዲዮላን ሲያሰናቡቱ እርሱን እንደሚተኩ ዋስትና ስላልሰጡት ነው።አርቴታ በአርሰናል በተጫዋችነት ለስድስት አመት መቆየቱ ይታወቃል ።
(Sunday Mirror)





ቶተንሀም ብራዚላዊውን የፍላሚንጐ አማካይ ጌርሰን በጥር ወር የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ጆዜ የ22 አመቱን አማካይ በጥብቅ ይፈልጉታል ።
(90min)





ኦሌ ጉናር ሶልሻየር ማን ዩናይትድ የ19 አመቱን ኖርዌያዊ የሬድ ቡል ሳልዝበርግ አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ ለማዘዋወር ከወኪሉ ሚኖ ራዮላ ጋር እየተነጋገረ  መሆኑን ይፋ አድርጓል ።
(Sunday Mirror)




ዴንማርካዊው የቶተንሀም አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን በጥር ወር የዝውውር መስኮት ወደ ማን ዩናይትድ የመሄድ ፍላጎት የለውም ።የ27 አመቱ ተጨዋች ኮንትራቱ ክረምት ላይ ይገባደዳል።
(Daily Star Sunday)






ጋቦናዊው የ30 አመት ኢንተርናሽናል ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ በአርሰናል ለመቆየት ከሚፈልጉ ተጨዋቾች ውስጥ ነው።ኦባማያንግ ምንም ያህል ብዙ ፈላጊዎች ቢኖሩትም በመድፈኞቹ ቤት ደስተኛ ነው።
(Independent)





የቶተንሃሙ ፕሬዝደንት ዳኒ ሌቪ በቅርቡ በአንድ ቢሊየን ፓውንድ የጨረሱትን ስቴዲየም ስያሜ ሊያከራዩት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ስፐርስ ከስቴዲየሙ ስያሜ ሪከርድ የሆነ £25ሚ.  በየዓመቱ እንደሚያገኝ ይጠበቃል፡፡
(Telegraph)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...