Saturday, December 14, 2019

የእሁድ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                       አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)

የሬድ ቡል ሳልዝቡርጉ የ19 አመት ኖርዌያዊ አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ ከበርካታ ክለቦች የዝውውር ጥያቄ ቢቀርብለትም እርሱ ግን መሄድ የሚፈልገው ወደ ሀገሩ ልጅ ኦሌ ጉናር ሶልሻየር ክለብ ማን ዩናይትድ ነው።
(Star on Sunday)




ባርሴሎና ፔፕ ጋርዲዮላ በአመቱ መጨረሻ ከማንቸስተር ሲቲ የሚለቅ ከሆነ የኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ተተኪ ማድረግ ይፈልጋል።ፔፕ ዘንድሮ ዝቅተኛ አጀማመር በውሃ ሰማያዊዎቹ ቤት ያደረገ ሲሆን ከሊቨርፑል ጋር ማን ሲቲ ያለው ልዩነትም አስራ ሰባት ነጥብ ደርሷል።
(Sunday Express)





ማንቸስተር ሲቲ ፥ ማንቸስተር ዩናይትድ ፥ ሊቨርፑል እና ቼልሲ እንግሊዛዊውን የ19 አመት አጥቂ ጄደን ሳንቾ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ለዝውውሩ £90ሚ. ይፈልጋል።
(Sun on Sunday)





ጆዜ ሞሪንሆ ከክሪስቲያን ኤሪክሰን ጋር ንግግራቸውን እንዳጨረሱ ተናግረዋል።ፖርቱጋላዊው አሰልጣኝ ስፐርስን ከያዙ ጀምሮ ከተጨዋቹ ጋር ውዝግብ ውስጥ  የገቡ ሲሆን በቀሪ የክለብ ቆይታው ጉዳይ እየተነጋገሩ መሆናቸውን ጆዜ ተናግረዋል።
(Sunday Mirror)




በሪያል ማድሪድ የተጠበቀውን ያህል ያልሆነው ቤልጄሚያዊው የ28 አመት አጥቂ ኤድን ሀዛርድ በበርናቢዮ ያለው ኮንትራት ሲያበቃ ወደ ቼልሲ መመለስ ይፈልጋል።
(Sun on Sunday)



ፈረንሳዊው ድንቅ አማካይ ንጎሎ ካንቴ ከቼልሲ መልቀቅ ይፈልጋል።የ28 አመቱ ካንቴ ምንም እንኳን የሀገሩ ልጅ ኦስማን ዴምቤሌ ወደ ባርሴሎና እንዲመጣ ቢነግረውም እርሱ ግን ጁቬንትስ አሊያም ሪያል ማድሪድ መሄድ ነው የሚፈልገው።
(Eldesmarque)



ማን ዩናይትድ ቤልጄሚያዊውን የናፖሊ አጥቂ ድረስ መርቲንስ የማዘዋወር ፍላጎት አለው፡፡ተጨዋቹ 32 አመቱ ነው።
(Tuttomercato)




ኪልያን ምባፔ በክለቡ ፓሪሰን ዤርመን ደስተኛ እንዳልሆነ እየተነገረ ቢሆንም የሪያል ማድሪዱ አለቃ ዚነዲን ዚዳን ስለዚህ ጉዳይ አስተያየት መስጠት እንደማይፈልግ ተናግሯል።ሎስብላንኮዎቹ የ20 አመቱ ፈረንሳዊ ዋነኛ ፈላጊ ናቸው፡፡
(Goal.com)





ብራዚላዊው አጥቂ ጋብሬል ጄሱስ የማን ሲቲው ምክትል አሰልጣኝ ማይክል አርቴታ ምርጥ የአሰልጣኝነት ብቃት አለው ሲል ተናግሯል።አርቴታ ስሙ በስፋት ከቀድሞው ክለቦች አርሰናል እና ኤቨርተን ጋር በመያያዝ ላይ ይገኛል።
(Manchester Evening News)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...